Fana: At a Speed of Life!

በመተከል ዞን ከ1 ሺህ በላይ ታጣቂዎች ትጥቃቸውን ፈተው እርቅ አካሄዱ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 3፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ማንዱራና ዳንጉር ወረዳዎች ከ3 ዓመታት በላይ ታጥቀው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ከ1 ሺህ በላይ አመራሮችና አባላት በጉሙዝ ብሔረሰብ ዕርቀ ሰላም ባህል መሠረት ትጥቃቸውን አስረክበው እርቅ አካሄዱ፡፡
የመተከል ዞን የተቀናጀ ኮማንድ ፖስት ዋና አስተባባሪ ሌተናል ጀኔራል ደስታ አብቼ÷ በደም የተፃፈና የታሰረ ቃለ መሃላ መፈፀሙ ታጣቂዎቹ ለሰላም ቁርጠኛ መሆናቸውን ያሳየ መሆኑን ገልጸዋል።
ሁሉም ለፈፀሙት ቃለ መሃላ በመገዛት ዘላቂ ሰላምን በማስፈን በተግባር እንዲያሳዩ አሳስበዋል፡፡
በሌሎች ወረዳዎች የሚገኙ ህገወጥ ታጣቂዎችም÷ የአፍራሽ ኃይሎችን ተልዕኮ ከማስፈፀም ተቆጥበው ቅድሚያ ለሰላም ዕድል እንዲሰጡ ኮማንድ ፖስቱ ጥሪ አቅርቧል፡፡
የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ጌታሁን አብዲሳ በበኩላቸው÷ በደምና በአጥንት የተዋሃድን ወንድማማች በመሆናችን ችግሮቻችንን ባሉን ባህልና ዕሴት መፍታት ይገባናል ማለታቸውን የመከላከያ ሰራዊት መረጃ ያመላክታል፡፡
ታጣቂዎቹ ለዚህ ዕርቀ ሰላም እንዲበቁ ከፍተኛ ጥረት ያደረገው ኮማንድ ፖስት፣ የሀገር ሽማግሌዎች እና የሃይማኖት አባቶች ተመስግነዋል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.