Fana: At a Speed of Life!

በመተከል ያለውን የፀጥታ ችግር ከመሠረቱ ለመፍታት የተቀናጀ ኃይል እንዲሠማራ ተደርጓል -ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ

አዲስ አበባ፣ታህሳስ 15፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) በቤኒሻንጉል ክልል በመተከል ዞን ያለውን የፀጥታ ችግር በተለያየ መንገድ ለመፍታት የተደረገው ጥረት የሚፈለገውን ውጤት ባለማምጣቱ ችግሩን ከመሠረቱ ለመፍታት የተቀናጀ ኃይል እንዲሠማራ ተደርጓል አሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ፡፡

በቤኒሻንጉል ክልል መተከል ዞን በዜጎች ላይ እየተፈጸመ ያለው ጭፍጨፋ እጅግ አሳዛኝ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ገልፀዋል፡፡

በወገኖቻችን ላይ በተፈጸመው ኢሰብአዊ ተግባር በእጅጉ አዝኛለሁም ብለዋል።

ችግሩን በተለያየ መንገድ ለመፍታት ያደረግነው ጥረት የሚፈለገውን ውጤት አላመጣም ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የጠላቶቻችን ዓላማ በጁንታው ላይ የሠነዘርነውን ብርቱ ኃይል ለመበተን ነው ሲሉ በማህበራዊ ገፃቸው ገልፀዋል።

ይህ የሚሳካ አይደለም ሲሉም አብራርተዋል።

መንግሥት ችግሩን ከመሠረቱ ለመፍታት አስፈላጊውን የተቀናጀ ኃይል እንዲሠማራ አድርጓልም ነው ያሉት።

የሚፈለገውን ውጤት ለማግኘት ሁሉም እንደ ከዚህ ቀደሙ በትኩረትና በኅብረት እንዲሠራ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.