Fana: At a Speed of Life!

በመንግስት መስሪያ ቤቶችና የልማት ድርጅቶች ተይዘው እስካሁን ያልለሙ ቦታዎች ግንባታ ሊካሄድባቸው ነው

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 7፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በፌዴራል መንግስት መስሪያ ቤቶችና የልማት ድርጅቶች ተይዘው እስካሁን ያልለሙ ቦታዎች ግንባታ ሊካሄድባቸው መሆኑን የመሬት ባንክና ልማት ኮርፖሬሽን አስታወቀ።
የኮርፖሬሽኑ ዋና ዳይሬክተር ሌንሣ መኮንን እንደገለጹት፥ በፌዴራል መንግስት መስሪያ ቤቶችና የልማት ድርጅቶች ተይዘው እስካሁን ያልለሙ ቦታዎች ላይ የተለያዩ ፕሮጀክቶችን ለመገንባት ታቅዷል።
በመሆኑም በመጪዎቹ አምስት ዓመታት 18 የተለያዩ ፕሮጀክቶች የሚገነቡ ሲሆን፥ በተያዘው በጀት ዓመት ደግሞ የሶስት ፕሮጀክቶች ግንባታ ይጀመራል ተብሏል።
ለዚህም ከሀገር ውስጥና ከውጭ ሀገራት ፕሮጀክቶቹን በፍጥነት እና ጥራት ማልማት የሚችሉ ባለሃብቶችን ለመሳብ እየተሰራ መሆኑን አብራርተዋል።
የሚገነቡት ፕሮጀክቶች በጤና፣ በቱሪዝም፣ በሆቴል፣ በግብርና፣ በቤቶች ግንባታና በትምህርት ዘርፎች ላይ መሆኑንም የሚከናወኑ መሆናቸውንም ዋና ዳይሬክተሯ ገልጸዋል።
የፕሮጀክቶቹ መገንባት ለተለያዩ ሴክተሮች አቅም ማጠናከሪያ እንዲሁም ለሀገሪቷ የኢኮኖሚ ግንባታ ወሳኝ መሆናቸውንም ጠቅሰዋል።
ለግንባታው ተጨማሪ ሃብት ማስገባት የሚችሉ አልሚዎችን ማሳተፍ ዋነኛው ትኩረት ይሆናልም ነው ያሉት።
የመሬት ባንክና ልማት ኮርፖሬሽን በዛሬው ዕለት “በፕሮጀክት መገምገሚያ ቀመር” ዙሪያ ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት ማድረጉንም ኢዜአ ዘግቧል።
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.