Fana: At a Speed of Life!

በመኖሪያ ቤታቸው የጦር መሳሪያ ተገኝቶባቸዋል የተባሉ ሁለት ግለሰቦች ላይ ለዐቃቤ ህግ ክስ የመመስረቻ የ15 ቀን ጊዜ ተፈቀደ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 26 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ፍርድ ቤቱ በመኖሪያ ቤታቸው በርካታ የጦር መሳሪያዎች ተገኝቶባቸዋል የተባሉ ሁለት ግለሰቦች ላይ ለዐቃቤ ህግ ክስ የመመስረቻ የ15 ቀን ጊዜ ፈቀደ።

ክስ መመስረቻ ጊዜ የተጠየቀባቸው ተጠርጣሪዎች ደፋር ተሰማ እና ገብረመስቀል ወልደምህረት ይባላሉ።

የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ወንጀል ምርመራ ዘርፍ መርማሪ ፖሊስ 1ኛ ተጠርጣሪ ደፋር ተሰማ በተጠረጠረበት ህገ መንግስታዊ ስርአቱን በሃይል ለመናድ ሙከራ ወንጀል ከኦነግ ሸኔ ጋር ግንኙነት በማድረግ ተልዕኮ ተቀብሎ ሲንቀሳቀስ እና በሰንዳፋ በሚገኘው መኖሪያ ቤቱ በተደረገ ብርበራ በርካታ ክላሾች የጦር መሳሪያ መያዙን ለፍርድ ቤት በመግለጽ ከሶስት በላይ ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ መጠየቁ የሚታወስ ነው።

በተመሳሳይ በአዲስ አበባ ከተማ ከህወሓት ጸረሰላም ቡድን በተሰጠው ተልዕኮ ጥቃት ለመፈጸም በመኖሪያ ቤቱ የጦር መሳሪያዎች ተገኝቶበታል የተባለው ገብረመስቀል ወልደ ምህረት የተባለው ግለሰብ ከሶስት ጊዜ በላይ ፍርድ ቤት ቀርቦ ምርመራ ሲከናወንበት ቆይቷል።

ይሁንና መርመሪ ፖሊስ በዛሬው ችሎት ምርመራውን ማጠናቀቁን ተከትሎ የምርመራ መዝገቡን ለዐቃቤ ህግ ማስረከቡን ለችሎቱ አስታውቋል።

በችሎቱ የተሰየመው ጠቅላይ ዐቃቤ ህግም በግለሰቦቹ ላይ መዝገቡን መርምሮ ክስ ለመመስረት በስነ ስርአት ህጉ መሰረት 15 ክስ መመስረቻ ቀን እንዲሰጠው ችሎቱን ጠይቋል።

ተጠርጣሪዎቹ በበኩላቸው የቤተሰብ አስተዳዳሪ መሆናቸውን በመጥቀስ በዋስ እንዲወጡ ጠይቀዋል።

የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ 1ኛ ጊዜ ቀጠሮ ችሎትም ለዐቃቤ ህግ ክስ መመስረቻ 15 ቀን ፈቅዷል።

በዚህ ጊዜ ዐቃቤ ህግ ክስ ካልመሰረተ በሌላ መዝገብ ተጠርጣሪዎቹ መብታቸውን መጠየቅ እንደሚችሉ ገልጿል።

በታሪክ አዱኛ

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳ
የፋና ድረ ቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.