Fana: At a Speed of Life!

በመከላከያ ሰራዊት ላይ ጥቃት እንዲደርስ የመሩና ያቀናጁ የሕወሃት አመራሮች ለዚህ ሁሉ ጥፋት ተጠያቂ ናቸው-የቀድሞ የሕወሃት ታጣቂዎች

በመከላከያ ሰራዊት ላይ ጥቃት እንዲደርስ የመሩና ያቀናጁ የሕወሃት አመራሮች ለዚህ ሁሉ ጥፋት ተጠያቂ ናቸው-የቀድሞ የሕወሃት ታጣቂዎች

አዲስ አበባ ፣ ጥር 16 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በመከላከያ ሰራዊት የሰሜን እዝ ላይ ጥቃት እንዲደርስ የመሩና ያቀናጁ የሕወሃት አመራሮች ለዚህ ሁሉ ጥፋት ተጠያቂ መሆናቸውን የቀድሞ የሕወሃት ታጣቂዎች ተናገሩ።

የህወሃት ቡድን በኢትዮጵያ ታሪክ ተፈፅሞ የማያውቅ ክህደት መፈፀሙንም ገልጸዋል።

የሕወሃት ጁንታ ለእኩይ ተልዕኮ ቢያሰልፋቸውም “መከላከያ ሰራዊትን አንወጋም” በሚል እጃቸውን ለሰራዊቱ ከሰጡ የልዩ ሃይል ፖሊስ አባላት መካከል አብርኸት መውጫና ትዝታ ካሳሁን ይገኙበታል።

በቁጥጥር ስር በዋሉበት ወቅት የሕወሃት ጽንፈኛ ቡድን የደሃ ልጆችንና እድሜያቸው ለውጊያ ያልደረሱ ታዳጊዎችን በማስገደድ ለውጊያ ማሰለፉን በማውገዝ የጁንታውን እኩይ አላማ ማውገዛቸውም ይታወቃል።

ወጣቶቹ ላለፉት ሁለት ወራት በብሔራዊ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ድጋፍ በአዋሽ አርባ በሚገኘው የደቡብ ዕዝ ማሰልጠኛ ማዕከል የተሃድሶ ስልጠና ላይ ይገኘሉ።

አበርኸት እና ትዝታም ስልጠናው ሲሳቸው ከነበሩ ከ750 በላይ የቀድሞ የሕወሃት ልዩ ሃይል፣ ፖሊስና ሚሊሻዎች መካከል ይገኙበታል።

በተሃድሶ ስልጠና ቆይታቸው አስፈላጊው ግብዓት እንደተሟላላቸውና በመከላከያ ሰራዊት እንክብካቤ ሲደረግላቸው መቆየቱንም ያስረዳሉ።

ከአብርኸትና ትዝታ በተጨማሪ ከመከላከያ ተሰናብቶ በክልሉ ልዩ ሃይል አባል የነበረው ተስፋዬ ጥላሁን፣ እንዲሁም የሚሊሻ አባላት የነበሩት አቶ ሞላ ነጋልኝና አቶ ይብራ ሃይለስላሴም አያያዛቸው መልካም አንደሆነ ገልጸዋል።

በተሃድሶ ስልጠና ላይ የቆዩት ታጣቂዎቹ በሕወሃት ሰዎች መጠቀሚያ መሆናቸው እንዳስቆጫቸው ገልፀው፤ በመከላከያ ሰራዊት የሰሜን እዝ ላይ የተፈጸመው ጥቃትም ታሪካዊ ስህተት መሆኑን አንስተዋል።

ለዚህ ድርጊት የሕወሃት ፅንፈኛ ቡድን አመራሮች ጠንሳሽና አስፈፃሚዎች እንደነበሩ አስታውሰው ለደረሰው ጥፋት ሁሉ ዋነኛ ተጠያቂዎች ናቸው ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.