Fana: At a Speed of Life!

በመካነ ሠላም ከተማ የተከሰተ የእሳት አደጋ በንብረት ላይ ጉዳት አደረሰ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 6 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአማራ ክልል ደቡብ ወሎ ዞን መካነ ሠላም ከተማ የተከሰተ የእሳት አደጋ በንብረት ላይ ጉዳት አድርሷል፡፡
የእሳት አደጋው የተከሰተው ትናንት በግምት ከቀኑ 10 ሰዓት ከ30 አካባቢ በተለምዶ ቦለቄ ሰፈር እየተባለ በሚጠራው አካባቢ መሆኑ ታውቋል፡፡
አደጋውም ጫማ ቤቶች ላይ ጉዳት አድርሷል፡፡
የእሳት አደጋውን በህብረተሰቡ ርብርብ የከፋ ጉዳት ሳያደርስ መቆጣጠር ተችሏል ነው የተባለው፡፡
የአደጋው መንስኤ የኤሌክትሪክ አደጋ መሆኑን የገለፀ ሲሆን የከተማ አስተዳደሩ ፖሊስ ጽህፈት ቤት የጉዳት መጠኑን እያጣራ መሆኑን ከመካነ ሠላም ከተማ ኮሙዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.