Fana: At a Speed of Life!

በመደበኛ የ24 ሰዓት ዕለታዊ መግለጫ ከተገለፀው በተጨማሪ በአማራ ክልል አራት ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኘባቸው

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 14 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የጤና ሚኒስቴር በመደበኛ የ24 ሰዓት ዕለታዊ መግለጫ ከተገለፀው የላቦራቶሪ ምርመራ በተጨማሪ በአማራ ክልል አራት ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው አስታወቀ።

ሚኒስቴሩ በክልሉ ለ41 ሰዎች የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጎ ተጨማሪ አራት ሰዎች ላይ ቫይረሱ መገኘቱን ነው ያስታወቀው።

ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ሁሉም ወንድ ሲሆኑ እድሜያቸው ከ29 እስከ 97 አመት የሚገኙ ናቸው።

ነዋሪነታቸውም ሁለቱ ምዕራብ ጎንደር ሲሆን፥ ሁለቱ ደግሞ በማዕከላዊ ጎንደር እና ጎንደር ከተማ ነዋሪዎች መሆናቸው ተገልጿል።

ከዚህ ውስጥ አንደኛው ግለሰብ የውጭ ሃገር የጉዞ ታሪክ ያለው ሲሆን፥ ሶስቱ ግለሰቦች የውጭ ሃገር የጉዞ ታሪክ የሌላቸውና የውጭ ሃገር የጉዞ ታሪካቸው በመጣራት ላይ ያለ ነው ተብሏል።

ይህን ተከትሎም ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ 34 ሰዎች በምርመራ የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል ብሏል።

ሚኒስቴሩ ምሳ ሰአት ላይ ባለፉት 24 ሰአታት ለ3 ሺህ 645 ሰዎች የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 30 ሰዎች ቫይረሱ እንደተገኘባቸው መግለጹ ይታወሳል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.