Fana: At a Speed of Life!

በመዲናዋ ለህዳሴ ግድብ በሶስት ወራት ውስጥ ከ600 ሚሊየን ብር በላይ ተሰብስቧል

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 22፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የህዳሴ ግድብ ዋንጫ በአዲስ አበባ የተለያዩ ክፍለ ከተሞች እየተዘዋወረ ነው፡፡
ዋንጫው ባለፉት 15 ቀናት ኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ የቆየ ሲሆን በዚህ ጊዜም ከ123 ሚሊየን ብር በላይ መሰብሰብ መቻሉ ተገልጿል።
አሁን ላይም ዋንጫውን አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ የተረከበ ሲሆን ለቀጣዮቹ ሁለት ሳምንታት በክፍለ ከተማው የሚቆይ ይሆናል።
በክፍለ ከተማው በሚኖረው ቆይታም ለግድቡ ግንባታ የሚውል ከ100 ሚሊየን ብር በላይ ለመሰብሰብ ዕቅድ መያዙ ታውቋል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በበጀት አመቱ ለህዳሴው ግድብ 700 ሚሊየን ብር ለመሰብሰብ አቅዶ ባለፉት ሶስት ወራት ብቻ ከ600 ሚሊየን ብር በላይ መሰብሰብ መቻሉን በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የመንግስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት አስተባባሪ አቶ ጃንጥራር አባይ መነገራቸውን ኢቢሲ ዘግቧል።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.