Fana: At a Speed of Life!

በመዲናዋ ለተማሪዎች ፣ለመምህራንና ለትምህርት ዘርፍ አመራሮች የሽልማት እና የእውቅና መርሐግብር ተካሄደ 

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 1 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)በአዲስ አበባ ከተማ የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ የ10ኛ እና 12 ኛ ክፍል ተማሪዎች ፣መምህራንና የትምህርት ዘርፍ አመራሮች የሽልማት እና የእውቅና መርሐግብርተካሂዷል፡፡
በወዳጅነት አደባባይ በተካሄደው በዚህ መርሃ ግብር የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤን ጨምሮ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የመንግስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት አስተባባሪ አቶ ጃንጥራር አባይ፣ መምህራን፣ተማሪዎች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል፡፡
በመርሃ ግብሩ በ2012ዓ.ም የትምርት ዘመን በዘርፉ የተሰሩ ስራዎች እንዲሁም አሁን በመሰራት ላይ ያሉ ስራዎች ተገልፀዋል፡፡
ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ በመርሐ ግብሩ በ2012 በጀት አመት የተከሰተው የኮቪድ 19 ወረርሽኝ ያስከተለውን ችግርን በመቋቋም ጥናትን መሰረት ያደረገ ስትራተጂዎችን በመንደፍ ተማሪዎች እንዲማሩ ለማድረግ ከፍተኛ ጥረት ተደርጓል ብለዋል ።
በአጠቃላይ በዛሬው እለት የከተማ አስተዳደሩ 4 ሺህ 187 ለሚሆኑ በ2012 የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና እና በ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ከፍተኛ ውጤት ላያስመዘገቡ እንዲሁም በ2013 የትምህርት ዘመን በአጠቃላይ ትምህርት የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎችና ለመምህርን፣የትምህርት ዘርፍ ባለሙያዎች እና አመራሮች የእውቅና ሽልማት ሰጥቷል፡፡
በፌቨን ቢሻው
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.