Fana: At a Speed of Life!

በመዲናዋ ለገና በዓል የሚሆን የግብርና ምርቶች፣ የእንስሳት ተዋጽዖ እና የፍጆታ እቃዎችን ለህብረተሰቡ ለማቅረብ በቂ ዝግጅት ተደርጓል-ኤጀንሲው

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 24 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ ለገና በዓል የሚሆን የግብርና ምርቶችን ጨምሮ የተለያዩ የእንስሳት ተዋጽዖ እና የፍጆታ እቃዎችን በተመጣጣኝ ዋጋ ለህብረተሰቡ ለማቅረብ በቂ ዝግጅት መደረጉን  የከተማዋ ህብረት ስራ ኤጀንሲ አስታወቀ፡፡ ።

የህብረት ስራ ኤጀንሲው ከገና በዓል ጋር ተያይዞ የገቢያ የዋጋ ንረት እንዳይፈጠር የተለያዩ የግብርና እና የኢንዱስትሪ ምርቶችን ለሸማቹ ማህበረሰብ በተመጣጣኝ ዋጋ ለማቅረብ የቅድመ ዝግጅት ስራውን መጠናቀቁን የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ውብነህ እምሩ አስታውቋል፡፡

ኤጀንሲው ከኦሮሚያ እና አማራ ክልሎች ከሚገኙ አምራች ዩኒየኖች ጋር የገቢያ ትስስር በመፍጠር 19 ሺህ ኩንታል በላይ ጤፍ ፣ 4 ሺህ ኪሎ ቀይ ሽንኩርት፣ ከ180 የበላይ የእርድ በሬዎች፣ ከ1ሚሊየን በላይ እንቁላል እንዲሁም ከ1 ሚሊየን ሊትር በላይ ዘይት እና ከ3 ሺህ 500 ኪሎ ግራም በላይ የቅቤና አይብ ምርቶችን በተመጣጣን ዋጋ ለሸማቹ ለማቅረብ መዘጋጀታቸውን ዋና ዳይሬክተሩ ተናግረዋል፡፡

በተጨማሪም በአስሩም ክፍለከተሞች ከሚገኙ የህብረት ስራ ማህበራት ሱቆች ባለፈ በተለያዩ ቦታዎች በተለይ ጉለሌ፣ በአራት ኪሎ፣አየር ጤና፣ኮልፌ አካባቢና 18 ማዞርያ አካባቢ ለዶሮ እና እንቅላል የመሸጫ ቦታዎች መዘጋጀታቸውን አቶ ውብነህ መናገራቸውን ከአዲስ አበባ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ያገኘኘው መረጃ ያመለክታል።

ሸማቹ ማህበረሰብም በበዓል ግብይት ወቅት እራሱን ከኮቪድ19 ወረርሽን በጠበቀ መልኩ እንዲገበያይ ዋና ዳይሬክተሩ አሳስበዋል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳ

የፋና ድረ ቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.