Fana: At a Speed of Life!

በመዲናዋ ለጽዳት ባለሞያዎች ነጻ የትራንስፖርት አገልግሎት እንዲዘጋጅ ተወሰነ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 9፣ 2013(ኤፍ ቢሲ) የከተማ የጽዳት ሰራተኞችን ለማመስገን እና ክብር ለመስጠት ልዩ የምስጋና እና የምሳ መርሃግብር ተካሂዷል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ የሌሊት ጨለማ ፣ ብርድ ፣ ዝናብ ፣ ፀሃይ እና መጥፎ ሽታ ሳይሉ ለከተማዋ ጽዳት ቀን ከሌሊት ለሚተጉት የጽዳት ሰራተኞች ዛሬ የከተማ አስተዳደሩ ልዩ የምስጋና እና የምሳ መርሃግብር አዘጋጅቷል ብለዋል፡፡
እነዚህ የከተማዋ ያልተዘመረላቸው ጀግኖችን ማመስገን እና ክብር መስጠት ለሁላችንም ክብር ነው ያሉት ምክትል ከንቲባዋ የከተማ አስተዳደሩም ስራቸውን በማክበር ነጻ የትራንስፖርት አገልግሎት እንዲዘጋጅ መወሰኑን አስታውቀዋል፡፡
ከጽዳት ሰራተኞች መካከል 80 በመቶ እናቶች በመሆናቸው ይህ የትራንስፖርት አገልግሎት ተጋላጭነታቸውን ይቀንሳልም ብለዋል፡፡
ልፋታቸውን የሚመጥን ክብር እና ድጋፍ መስጠት ከሁሉም የሚጠበቅ መሆኑን በማንሳትም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አንስተዋል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.