Fana: At a Speed of Life!

በመዲናዋ በልማታዊ ሴፍቲኔት መርሃ ግብር ከ40 ሺህ በላይ ዜጎች ተጠቃሚ ሆነዋል

አዲስ አበባ፣ የካቲት 6፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ በምግብ ዋስትና ልማታዊ ሴፍቲኔት መርሃ ግብር ከ40 ሺህ በላይ ዜጎች በአማራጭ ገቢ ማስገኛ ተጠቃሚ መሆናቸውን የአዲስ አበባ ከተማ ምግብ ዋስትና እና ልማታዊ ሴፍቲኔት ኤጀንሲ ገለፀ።

ኤጀንሲው በአካባቢ ጥበቃ ስራ፣ በከተማ ግብርና እና በጽዳት አገልግሎት ስራ ላይ እንዲሰማሩ በማድረግ 40 ሺህ 797 ዜጎችን ተጠቃሚ ማድረጉን አስታውቋል።

ከዚህ በተጨማሪም በሴፍቲኔት መርሃ ግብር ታቃፊ ከሆኑ የቤተሰብ አባላት ተማሪዎች ውስጥ 60 ሺህ 348 የትምህርት፣ የምገባ እና የትምህርት መሳሪያ ቁሳቁሶች ተጠቃሚ መሆን ችለዋል ብሏል።

እንዲሁም መርሃ ግብሩ ተግባራዊ ከተደረገበት ግንቦት ወር 2009 ዓ.ም ጀምሮ በሶስት ዙር ከ400 ሺህ በላይ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ ነዋሪዎች ተጠቃሚ ሆነዋልም ነው ያለው።

በተጨማሪም በመጀመሪያው ዙር ተጠቃሚ ከሆኑት ከ123 ሺህ የህብረተሰብ ክፍሎች ውስጥ ከ29 ሺህ በላይ የቤተሰብ ተወካይ በመምረጥ፥ የንግድ ስራ እቅድ በማዘጋጀት በቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች በተለያዩ ዘርፎች ስልጠና እየወሰዱ እንደሚገኙ ከአዲሰ አበባ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.