Fana: At a Speed of Life!

በመዲናዋ በተያዘው ክረምት ከ7 ነጥብ 4 ሚሊየን በላይ ችግኝ ለመትከል ዝግጅት ተደርጓል- አስተዳደሩ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 7፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከተማ ውበትና አረንጓዴ ልማት ቢሮ በተያዘው በ2014ዓ.ም ክረምት የአረንጓዴ አሻራ ልማት መርሃ ግብር ከ7 ነጥብ 4 ሚሊየን በላይ ችግኝ ለመትከል በዘጠኝ ችግኝ ጣቢያዎች ችግኝ የማፍላት የቅድመ ዘግጅት መደረጉን አስታወቀ፡፡

አስተዳደሩ እንዳለው ፥ እስካሁን ከ1 ነጥብ 4 ሚሊየን በላይ የችግኝ የጉድጓድ ቁፋሮ የቅድመ ዝግጅት ስራ ተጠናቋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከተማ ውበትና አረንጓዴ ልማት ቢሮ ምክትል ኃላፊ ወይዘሮ ይመኙሻል ታደሰ እንደገለጹት ፥ በክረምቱ ከሚተከለው 7 ነጥብ 4 ሚሊየን ችግኝ ውስጥ 20 በመቶ የሚሆነው የጓሮ አትክልትና ፍራፍሬ ነው ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አራተኛው የአረንጓዴ አሻራ ልማት ዘመቻ መርሐ ግብር ከሰኔ 18 እስከ 20 ቀን 2014 ዓ.ም ድረስ ሁሉም የህብረተሰብ ክፍሎች በተሳተፉበት እንደሚጀመርም ተገልጿል፡፡

ባለፈው ዓመት የአረንጓዴ አሻራ ልማት ከተተከሉት 26 ሚሊየን ችግኞች 80 በመቶ ችግኝ መጽደቁን የገለጹት ሃላፊዋ ፥ የተተከሉ ችግኞች ከተተከሉ በኋላም ማህበረሰቡ የባለቤትነት ጥበቃና እንክብካቤ እንዲያደርግላቸው ይደረጋል ማለታቸውን ከከተማው ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.