Fana: At a Speed of Life!

በመዲናዋ በተደረገ ብርበራ ለሽብር አገልግሎት ሊውሉ የነበሩ በርካታ የጦር መሣሪያዎች ተይዘዋል – ፖሊስ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 25፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ፖሊስ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን መሠረት በማድረግ ባደረገው ብርበራ ለሽብር አገልግሎት ሊውሉ የነበሩ በርካታ የጦር መሣሪያዎች መያዙን ገለጸ።
 
የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽነር ጌቱ አርጋው ÷አሸባሪዎቹ ህወሓት እና ሸኔ እንዲሁም ደጋፊዎቻቸው አዲስ አበባን ማዕከል ያደረገ ሁከት እና ብጥብጥ ለመፍጠር አቅደው ሲሠሩ የነበረ ቢሆንም የአዲስ አበባ ፖሊስ ከመላው የሀገሪቱ የፀጥታ ኃይሎች ጋር በመሆን የአሸባሪ ቡድኑን ዓላማ ማክሸፍ መቻሉን አንስተዋል።
 
አሸባሪው ህወሓት አዲስ አበባ ተከብባለች በማለት ሕዝቡን የሚያሸብር ፕሮፓጋንዳ እየነዛ ሲንቀሳቀስ ነበር ያሉት ኮሚሽነር ጌቱ ÷በተግባርም በዚህ ሂደት ውስጥ የተሳተፉ እና ለመሳተፍ የተዘጋጁ የጁንታው አባላት እንዳሉ ፖሊስ በሠራቸው ሥራዎች ለማረጋገጥ መቻሉን ጠቁመዋል።
 
ይህንን መነሻ በማድረግ በርካታ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ነው የተናገሩት።
 
ከዚህ ጎን ለጎን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን መሠረት በማድረግ በተደረገ ብርበራ ለሽብር አገልግሎት ሊውሉ የነበሩ 28 ቦምቦች፣ 65 ክላሽንኮቭ መሣሪያ፣ ከ5 ሺህ በላይ ጥይቶች እንዲሁም 272 ሽጉጦችን ከ3 ሺህ በላይ ጥይቶች እና ካርታዎች ጋር መያዝ ተችሏል በለዋል።
በተጨማሪም 2 ሺህ 889 የብሬን ጥይት፣ ተጥሎ የተገኘ 83 የዲሽቃ ጥይቶች፣ 42 የጦርሜዳ መነፅር፣ ከ50 በላይ የሬዲዮ መገናኛዎች እና ፈንጂዎች እንዲሁም በርካታ ወታደራዊ አልባሳት እና የደንብ ልብሶች መያዙን ገልጸዋል።
 
ለሽብር ዓላማ ሊውሉ የነበሩ ከ700 ሚሊየን ብር በላይ፣ 399 ሺህ 371 የአሜሪካ ዶላር፣ 26 ሺህ 755 ዩሮ፣ 19 ሺህ 788 ፓውንድ፣ 273 ሺህ 867 የተለያዩ ሀገራት ገንዘቦችም በተደረገው ብርበራ እንደተያዘ መናገራቸውን ከፌዴራል ፖሊስ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
 
የተለያዩ ሕገ-ወጥ ሰነዶች እና የባንክ ደብተሮች እንዲሁም ወደ ስምንት ኪሎግራም የሚመዝን የወርቅ እና የብር ጌጣ ጌጦች በተጠርጣሪዎች መኖሪያ ቤት በተደረገ ብርበራ መያዛቸውንም ኮሚሽነሩ አስታውሰዋል።
 
አካባቢዎን ይጠብቁ!
 
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
 
መከላከያን ይደግፉ!
 
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.