Fana: At a Speed of Life!

በመዲናዋ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የሁለት ሰዎች ህይወት አለፈ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 21፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ ጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ አንድ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የሁለት ሰዎች ህይወት ሲያልፍ በ11 ሰዎች ላይ ደግሞ ከባድና ቀላል የአካል ጉዳት ደርሷል፡፡
የትራፊክ አደጋው የደረሰው 13 ሰዎችን አሳፍሮ ከእንጦጦ ወደ ቁስቋም ይጓዝ የነበረ አነስተኛ የሕዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ገደል ውስጥ በመግባቱ ነው፡፡
በዚህም የሁለት ሰዎች ህይወት ሲያልፍ በ11 ሰዎች ላይ ከባድ እና ቀላል የአካል ጉዳት መድረሱን የጉለሌ ክፍለ ከተማ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡
የክፍለ ከተማው ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ጌታሁን አበራ÷ አሽከርካሪዎች በኃላፊነት ስሜት ፍጥነታቸውን ቀንሰው በማሽከርከር የዜጎችን ህይወትና ንብረት ከአደጋ መጠበቅ አለባቸው ብለዋል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.