Fana: At a Speed of Life!

በመዲናዋ በግማሽ ዓመቱ ለ104 ሺህ ወጣቶች የስራ ዕድል ተፈጠረ

አዲስ አበባ፣ ጥር 20፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ በግማሽ ዓመቱ ለ104 ሺህ ወጣቶች የስራ ዕድል መፈጠሩን የከተማዋ አስተዳደር የስራ እድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዝ ልማት ቢሮ አስታወቀ።

ቢሮው የስድስት ወራት እቅድ አፈጻጸሙን በገመገመበት ወቅት ከ125 ሺህ በላይ ስራ ፈላጊዎችን በመመዝገብ ለ104 ሺህ 587 የስራ እድል መፍጠር መቻሉን ገልጿል፡፡

በቀሪ ስድስት ወራትም ሰፊ ስራ እድል ለመፍጠር የስራ መስኮች ልየታ እና ስራ ፈላጊ ዜጎችን የመመዝገብ እና የመለየት ስራ እየተሰራ መሆኑንም ነው ያስታወቀው።

የተያዘውን እቅድ ለማሳካትም ስራ ሊፈጠርባቸው የሚችሉ አማራጭ የስራ መስኮች ልየታ ላይ መሆኑን ጠቅሶ፥ ከ53 በላይ የንግድ እቅድ እና ከ11 በላይ የቪዲዮ ፕሮቶታይፕ መዘጋጀቱን አስታውቋል፡፡

ቢሮው በ2012 በጀት ዓመት ለ250 ሺህ ዜጎች የስራ እድል ለመፍጠር ማቀዱን ከአዲስ አበባ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.