Fana: At a Speed of Life!

በመዲናዋ ከ1 ቢሊየን ብር በላይ ወጪ የተገነቡ የስፖርት ማዘውተሪያዎች ተመረቁ

 አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 4፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ ከ1 ቢሊየን ብር በላይ ወጪ የተገነቡ 51 የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች በምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ተመርቀዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለወጣቶች ልዩ ትኩረት በመስጠት የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎችን በማልማት የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራ ፕሮጀክቶችን እንዲጠናቀቅ አድርጓል ።
የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አፈጉባኤ ዘርፈሽዋል ንጉሴ ፣የመከላከያ ሚኒስቴር የኮንስትራክሽን ዘርፍ ሚኒስትር ዲኤታ አቶ ጌታቸዉ ኃይለማርያም ፣የአዲስ አበባ ስፖርት ኮሚሽነር በላይ ደጀን፣የስፖርት ቤተሰቦች እና የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት የስፖርት ማዘወተሪያ ስፍራዎቹ በይፋ ስራ ጀምሯል ።
 
የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች ከከተማ አልፈው ለሀገሪቱ የስፖርት ልማት እና ተተኪ ስፖርተኞችን ለማፍራት ትልቅ ጥቅም እንደሚኖራቸው ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ተናግረዋል ።
የከተማ አስተዳደሩ በ2013 በጀት ዓመት የወጣቶችና የስፖርት ቤተሰቡ ለረጅም ጊዜ ጥያቄዎችን መፍትሔ በመስጠት የስፖርት ልማት ፕሮጀክቶችን ጀምሮ በፍጥነት ማጠናቀቅ መቻሉን ከአስተዳደሩ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
 
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.