Fana: At a Speed of Life!

በመዲናዋ ከ150 በላይ ኢንተርፕራይዞች ወደ መካከለኛ ኢንዱስትሪ ሊሸጋገሩ ነው

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 29፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በዚህ ዓመት ከ150 በላይ ኢንተርፕራይዞች ወደ መካከለኛ ኢንዱስትሪ ለመሸጋገር እየተዘጋጁ መሆኑን የአዲስ አበባ የሥራ፣ ኢንተርፕራይዝና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ አስታወቀ።

በብረታ ብረትና የእንጨት ሥራ ንዑስ ዘርፍ የተደራጁና ለ11ኛ ጊዜ የሚመረቁ የማኑፋክቸሪንግ ኢንተርፕራይዞች የቢሾፍቱ አውቶሞቲቭ ኢንጂነሪንግና ማምረቻ ኢንዱስትሪን ጎብኝተዋል።

የአዲስ አበባ የሥራ፣ ኢንተርፕራይዝና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ የኢንተርፕራይዝ ድጋፍ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ፍስሐ ጥበቡ፥ የጉብኝቱ ዓላማ ኢንተርፕራይዞቹ በሽግግሩ ስኬታማ ሆነው አንዲሰሩ ለማስቻል መሆኑን ገልጸዋል።

በዚህም በዘንድሮው ዓመት መስፈርቱን ያሟሉ ከ150 በላይ ኢንተርፕራይዞች ወደ መካከለኛ ኢንዱስትሪ ለመሸጋገር መዘጋጀታቸውን ተናግረዋል።

ከሚሸጋገሩት ኢንተርፕራይዞች መካከል በቆዳ፣ በጨርቃ ጨርቅ፣ በብረታ ብረትና በእንጨት ስራዎች የተደራጁ ከ80 በላይ ሲሆኑ፥ ቀሪዎቹ ደግሞ በኮንስትራክሽን ዘርፍ የተደራጁ ናቸው።

በጉብኝቱ የመካከለኛ ኢንዱስትሪዎች ወደ ከፍተኛ ኢንዱስትሪ ለመሸጋገር ምን እንደሚያስፈልጋቸው ግንዛቤ የሚፈጥር መሆኑም ተገልጿል።

አብዛኛዎቹ ኢንተርፕራይዞች ወደ ከፍተኛ ኢንዱስትሪ መሸጋገር የሚያስችላቸው ሥራዎች ውስጥ እየገቡ ስለመሆኑም ገልጸዋል።

በ50 ሺህ ብር ካፒታል ተነስተው እስከ መካከለኛ የደረሱ 1 ሺህ 458 ኢንተርፕራይዞች በ10 ዙር መመረቃቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.