Fana: At a Speed of Life!

በመዲናዋ ወንጀል እየተፈጸመ ነው በሚል የውጭ ሃገራት ዜጎች ጉዞ እንዳያደርጉ በሚል የተናፈሰው ዜና ነባራዊ ሁኔታውን ያለገናዘበ ነው – ፖሊስ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 6 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ወንጀል በስፋት እየተፈፀመ ስለሆነ የውጪ ሀገራት ዜጎች ወደ ተጠቀሱት ስፍራዎች ጉዞ እንዳያደርጉ በማለት በአንዳንድ መገናኛ ብዙኃን እና ማህበራዊ ሚዲያዎች የተናፈሰው ዜና የከተማዋን ነባራዊ ሁኔታ ያላገናዘበ እንደሆነና የከተማችን የፀጥታ ሁኔታ አስተማማኝ መሆኑንም የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ገልጿል፡፡
ታህሳስ 18 ቀን 2013 ዓ/ም አንድ የውጪ ሀገር ዜጋ ከቤተሰቦቻቸው ጋር በመሆን ጉለሌ የዕፅዋት ማዕከልን በመጎብኘት ላይ እንዳሉ ስድስት ግለሰቦች በስለትና በዱላ በማስፈራራት ሁለት ቀለበት፣ 2 ሞባይልና 4ሺ ብር ቢወሰዱባቸውም ፖሊስ ባደረገው ክትትል ወንጀሉን ፈፅመዋል ያላቸውን ተጠርጣሪዎች በመያዝ ወንጀል የተፈፀመባቸው የውጪ ሀገር ዜጋ ተጠርጣሪዎቹን በአካል ቀርበው በመለየት እንዲያረጋግጡ ቢጠየቁም በልዩ ልዩ ምክንያት ያልቀረቡና ፖሊስ ከአካባቢው ሌሎች ተጨማሪ ማስረጃዎችን እያሰባሰበ መሆኑን አስታውቋል፡፡
ስፍራው በጣም ሰፊ እና ሰዋራ በመሆኑ መሰል የወንጀል ድርጊቶች ሊያጋጥሙ እንደሚችል የተፈፀመው የወንጀል ድርጊትም እየተጣራ መሆኑን አንዳንድ መገናኛ ብዙሃን ስለ አካባቢው የፀጥታ ሁኔታ ከኮሚሽኑ በቂ መረጃ ሳይጠይቁ በስማ በለው ያገኙትን መረጃ መነሻ በመድረግ የከተማችን ፀጥታ አስተማማኝ እንዳልሆነ በተለይ ደግሞ በእንጦጦ ፓርክ እና በአዲስ አበባ ዙሪያ መንቀሳቀስ ስጋት እንደሆነ አድርገው መዘገባቸው ተገቢነት የሌለው በመሆኑ ሊታረም ይገባል ብሏል፡፡
በቅርቡ የተከበረው የገና በዓል በሰላም መከበሩንና ከ12ሺህ በላይ ሰዎች የታደሙበት ታላቁ ሩጫ ያለምንም የፀጥታ ችግር መጠናቀቁ የከተማዋን ሰላማዊነት ማሳያ ስለመሆኑ ኮሚሽኑ አስታውሶ÷ በተጠቀሱት ስፍራዎች ያለው የፀጥታ ሁኔታ አስተማማኝ በመሆኑ ሰዎች በጋራም ሆነ በግል ጉብኝት እያደረጉ እንደሚገኙ ከአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.