Fana: At a Speed of Life!

በመዲናዋ ዘመናዊ የትራፊክ ቁጥጥር ስርዓት ተግባራዊ ሊደረግ ነው

አዲስ አበባ፣ የካቲት 19፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ የትራንስፖርት አገልግሎቱን ማሳለጥ የሚያስችል የኢንተለጀንት ትራፊክ ቁጥጥር ስርዓት ተግባራዊ ሊደረግ መሆኑ ተገለጸ።

ስርዓቱ በቅርብ ዓመታት ውስጥ ተግባራዊ እንደሚደረግ የከተማዋ ትራንስፖርት ባለስልጣን አስታውቋል።

ዘመናዊ የትራፊክ የቁጥጥር ስርዓቱ የዲዛይን ጥናት ጋኡፍ ኢንጂነሪንግ በተሰኘ የጀርመን ዓለም ዓቀፍ አማካሪ ድርጅት እየተከናወነ እንደሚገኝም ተገልጿል።

የዲዛይን ጥናቱ የከተማዋ አምስት ኮሪደሮችንና ከ200 በላይ የመንገድ መጋጠሚያዎችን ያካትታል ነው የተባለው።

የመጀመሪያ ኮሪደር የሆነው ከእንግሊዝ ኤምባሲ በድንበሯ ሆስፒታል – ጎላጎል አደባባይ – ኤድናሞል ያለው መንገድ የዲዛይን ስራው ተጠናቆ ከማህበረሰቡ ጋር ውይይት እየተደረገበት መሆኑ ተጠቁሟል።

ዘመናዊ የትራፊክ የቁጥጥር ስርዓቱ ተግባራዊ ሲደረግ አካል ጉዳተኞችን እና ሌሎች የህብረተሰብ ክፍሎችን በከፍተኛ ደረጃ ተጠቃሚ ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል።

ከዚህ ባለፈም አደጋዎችን ሊቀንሱ የሚችሉና የትራፊክ ፍሰቱን ሊያሻሽሉ የሚችሉ በድምፅ የሚሰሩ ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎች በአደባባዮችና በመንገድ መጋጠሚያዎች ላይ ይተከላሉ ነው የተባለው።

ወደ ስራ ሲገቡም በካሜራና በሌሎች ቴክኖሎጅዎች በመታገዝ በአንድ የቁጥጥር ማዕከል በቀላሉ ክትትል ይደረግባቸዋልም ተብሏል።

በሌላ በኩል የዲዛይን ስራው እንደየ አካባቢው ተጨባጭ ሁኔታ ደረጃውን የጠበቀ የፍሳሽ መስመር ዝርጋታን እንደሚያካትት ተመላክቷል።

በተጨማሪም ዲዛይኑ ዘመናዊ የእግረኛ መንገዶች፣ የታክሲ መጫኛና ማውረጃ ቦታዎች፣ የመዝናኛ ቦታዎችን እና ሌሎች አገልግሎቶችን ታሳቢ ያደረገ መሆኑን ከአዲስ አበባ መንገዶች ባለስልጣን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.