Fana: At a Speed of Life!

በመዲናዋ የሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች ነገ አሸባሪውን ሕወሃት በማውገዝ ሰልፍ ሊያካሂዱ ነው

አዲስ አበባ፣ ህዳር 24፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ)  በአዲስ አበባ የሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች በነገው እለት አሸባሪውን ህወሃት በማውገዝ ሰልፍ ያካሂዳሉ።

የሰልፉ አስተባባሪዎች ዛሬ በሰጡት መግለጫ የሽብር ቡድኑ ድርጊት የትግራይ ወጣቶችን እየነጠቀ እንደሚገኝ ነው የተናገሩት።

የሽብር ቡድኑ ለ27 ዓመታት በትግራይ ህዝብ ስም የነገደ እና የትግራይ ህዝብን የማይወክል መሆኑን ገልፀዋል።

በመሆኑም የትግራይ ወጣቶች የዚህ ሽብር ቡድን ድርጊት ህዝቡን የማይወክል በመሆኑ እጃቸውን ለመከላከያ ሰራዊት እንዲሰጥ አሳስበዋል።

በነገው ሰልፍም የአሸባሪውን ህወሃት ድርጊትን በማውገዝ የትግራይ ወጣቶች ይህን የሽብር ቡድን እምቢ እንዲሉ ጥሪ ያቀርባሉ ነው ያሉት።

በነገው እለት ከማለዳው 12 ሰዓት ጀምሮ በመዲናዋ የሚኖር መላው የትግራይ ተወላጅ በአበበ ቢቂላ ስታዲየም በመገኘት የሽብር ቡድኑን እንደሚያወግዙ አስታውቀዋል።

 

በታሪኩ ወልደሰንበት

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.