Fana: At a Speed of Life!

በመዲናዋ የትንሳኤ በዓል ያለምንም አደጋ ተከብሯል – የአዲስ አበባ እሳትና አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 16፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በመዲናዋ የትንሳኤ በዓል ምንም አይነት አደጋ ሳያጋጥም ተከብሮ መዋሉን የአዲስ አበባ እሳትና አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን አስታወቀ፡፡
በበዓሉ አከባበር ወቅት የእሳትና ድንገተኛ አደጋ መንስኤዎችን በቅጡ በመረዳት ማህበረሰቡ ያደረገው ጥንቃቄ ለበዓሉ ሰላማዊነት ትልቁን ድርሻ እንደሚይዝ የገለጸው ኮሚሽኑ÷ እንተቋምም የአደጋ መንስኤዎችን ሕዝቡ እንዲረዳና ጥንቃቄ እንዲያደርግ ቀደም ብሎ ግንዛቤ የመፍጠር ሥራ መከናወኑ ሌላኛው ምክንያት መሆኑ ተመላክቷል፡፡
በመሆኑም የማህበረሰቡ ጥንቃቄ ቀጣይነት እንዲኖረውና አደጋን የመቀነስ ሥራ የጋራ ኃላፊነት አድርጎ መውሰድ እንደሚገባ ያስገነዘበው ኮሚሽኑ÷ መጪው የኢድ በዓል ሲከበርም ተመሳሳይ ጥንቃቄዎች እንዲደረጉ አጽንኦት ሰጥቷል፡፡
በአዲስ አበባ በዋዜማው ከተከሰተው አንድ የእሳት አደጋ በስተቀር÷ በትንሳኤ በዓል ምንም አይነት አደጋ ሳይደርስ በሰላም መጠናቀቁን የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ ለዚኤዘ ተናግረዋል፡፡
የትንሳኤ ዋዜማ ምሽት ላይ በደረሰ የእሳት አደጋ ግምቱ 2 ነጥብ 4 ሚሊየን ብር የሚገመት ንብረት መውደሙን አስታውሰዋል፡፡
የእሳት አደጋው በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 በአንድ ጋራዥ ላይ መድረሱን ጠቅሰው÷ የንብረት ውድመት ከማስከተሉ በስተቀር በሰው ላይ ጉዳት አለማድረሱን አረጋግጠዋል፡፡
አደጋውን ለመቆጣጠር ሰባት የእሳት አደጋ ተሽከርካሪዎች እና 47 የህይወት አድን ሰራተኞች ተሰማርተው ባደረጉት ፈጣን ምላሽ እሳቱ ሳይዛመትና የባሰ ጉዳት ሳያደርስ ማጥፋት መቻሉንም ተናግረዋል።
አደጋውን ለመቆጣጠር በተደረገው ጥረት ከ65 ሚሊየን ብር በላይ የሚያወጣ ንብረት ማዳን መቻሉንም ጠቁመዋል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.