Fana: At a Speed of Life!

በመዲናዋ የኮቪድ19 መመሪያን በማይተገብሩ የምግብና መጠጥ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ላይ እርምጃ ሊወሰድ ነው

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 20 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በመዲናዋ የኮቪድ 19 መመሪያን በማይተገብሩ የምግብና መጠጥ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ላይ ህጋዊ እርምጃ እንደሚወስድ የአዲስ አበባ ምግብ፣መድሃኒት፣ጤና ክብካቤ፣ አስተዳደርና ቁጥጥር ባለስልጣን ገለፀ፡፡
 
የኮቪድ 19 ወረርሽኝ ወደ ኢትዮጵያ መግባቱን ተከትሎ በተለያዩ አገልግሎት ሰጪ ተቋማትና ህብረተሰብ በሚሰበሰብባቸው አካባቢዎች ቫይረሱን ለመከላከል የጥንቃቄ ተግባራት በስፋት ሲከናወኑ እንደነበር ይታወሳል።
 
በተለይ በምግብ ቤቶችና መጠጥ ቤቶች ውስጥ በአንድ ጠረጴዛ ከሶስት ሰው በላይ እንዳይቀመጥ በመመሪያ መከልከሉ ይታወቃል።
 
ህብረተሰቡም እጁን በተደጋጋሚ በመታጠብ፣ የእጅ ማፅጃ ኬሚካል በመጠቀም እንዲሁም የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ በማድረግ የጤና መመሪያውን ሲተገብር እንደነበር አይዘነጋም።
 
ሆኖም የቫይረሱ ስርጭት እየቀነሰ ነው በሚል የተሳሳተ ግንዛቤ ህብረተሰቡ ሲያደርጋቸው የነበሩ ጥንቃቄዎችን ወደ ጎን ማለቱ አሁን ላይ ዋጋ ማስከፈል ጀምሯል።
 
የአዲስ አበባ ምግብ መድሃኒት ጤና ክብካቤ አስተዳደርና ቁጥጥር ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር ትዕግስት በዳዳ ለኢዜአ እንዳሉት፥ የምግብና መጠጥ አገልግሎት የሚሰጡ ተቋማት የኮቪድ 19 ወረርሽኝ የጥንቃቄ መመሪያን በሚፈለገው ደረጃ ተግባራዊ እያደረጉ አይደለም፡፡
 
ባለስልጣኑም በአገልግሎት ሰጪ ተቋማት ላይ ሲያደርግ የነበረው ቁጥጥር መላላቱንም ነው የተናገሩት፡፡
 
ተቋማቱ የኮቪድ19 ወረርሽኝን ለመከላከል የወጣውን መመሪያ አክብረው እንዲሰሩ ባለስልጣኑ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎችን ሲያከናውን መቆየቱን አስታውሰዋል።
 
አሁን ላይ ወረርሽኙ አሳሳቢ ደረጃ ላይ በመድረሱ በዘመቻ መልክ ሁሉንም ተቋማት የማስገንዘብ ስራ እየተሰራ መሆኑን አስረድተዋል።
 
ባለስልጣኑ ከማስተማር ባሻገር በቀጣይ የኮቪድ 19 መመሪያን በማይተገብሩ ተቋማት ላይ እርምጃዎችን እንደሚወስድም ነው ያስጠነቀቁት።
 
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለ!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.