Fana: At a Speed of Life!

በመዲናዋ የድህረ ጦርነት ዝንፈቶችን ፈጥኖ ማረም በሚቻልበት ሁኔታ ላይ የመከረው ውይይት ተጠናቀቀ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 26 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ባለፉት ሶስት ቀናት በአዲስ አበባ በክፍለ ከተማ እና በወረዳ ደረጃ ባሉ አመራሮች የድህረ ጦርነት ዝንፈቶችን ፈጥኖ ማረም በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ሲከናወን የነበረው የውይይት መድረክ ተጠናቋል፡፡
የድህረ ጦርነት ዝንፈቶችን ፈጥኖ በማረም ሁለንተናዊ ድል እስከሚረጋግጥ በጦርነቱ ውስጥ የተገኙ ትሩፋቶችን አጠናክሮ የመጠበቅና የማስፋት ዓላማ የያዘው የውይይት መድረክ የ11ዱም ክፍለ ከተማና የወረዳ አመራር ማጠቃለያ ውይይት ተካሂዷል።
በክፍለ ከተማ እና በወረዳ ባሉ አጠቃላይ አመራር የኢትዮጵያን ህልውና ለማስጠበቅ ሲባል በተካሄደው ትግል የተገኙ አንጸባራቂ ድሎችን ማስጠበቅ በሚቻልበት ሁኔታ እና የድህረ ጦርነት ዝንፈቶችን ማረም በሚቻልበት ዙሪያ ውይይት ሲደረግ ቆይቷል ተብሏል።
ኢትዮጵያ ተገዳ የገባችበትን ጦርነት በውድ ልጆቿ መስዋዕትነት ድል ያስመዘገበች በመሆኑ የተገኘውን ድል መጠበቅና ማስፋት እንደሚገባ በውይይቱ ተገልጿል።
በማጠቃለያ ውይይቱ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ፣ የአዲስ አበባ ብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ መለሰ ዓለሙ እና የከተማዋ ምክትል ከንቲባ አቶ ጃንጥራር አባይ መገኘታቸውን ከአዲስ አበባ ፕሬስ ሴክረታሪ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.