Fana: At a Speed of Life!

በመዲናዋ 58 ሺህ ሀሰተኛ የብር ኖት ከ2 ተጠርጣሪዎች ጋር በቁጥጥር ስር ዋለ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 15፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ 58ሺህ ሀሰተኛ የብር ኖት ይዘው የተገኙ 2 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተጣራባቸው መሆኑን የከተማዋ ፖሊስ አስታወቀ፡፡
ከተጠርጣሪዎቹ መካከል አንደኛው በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 ልዩ ቦታው አውቶቡስ ተራ አካባቢ በቁጥጥ ስር መዋሉ ተገልጿል፡፡
ግለሰቡ በተጠቀሰው ስፍራ በሚገኝ ምግብ ቤት ውስጥ ገብቶ አገልግሎት ካገኘ በኋላ÷ ሀሰተኛ ባለ 200 የብር ኖት አውጥቶ ሲከፍል የምግብ ቤቱ ባለቤት የብሩን ትክክለኛነት ተጠራጥረው ለፖሊስ በሰጡት ጥቆማ እጅ ከፍንጅ ተይዟል፡፡
ግለሰቡ በያዘው ፌስታል ላይ በተደረገ ፍተሻም÷ በባለ 200 የብር ኖት 57 ሺህ 6 መቶ ሀሰተኛ ብር መገኘቱን ፖሊስ ገልጿል፡፡
በተጠርጣሪው ላይ በተደረገ ምርመራ በሀሰተኛ ገንዘብ ግብይት ፈፅሟል የተባለ ሌላ ግለሰብ እንደተያዘ እና ከግለሰቡ ኪስ ውስጥ ሀሰተኛ ባለ 200 የብር ኖት መገኘቱን የአዲስ አበባ ፖሊስ መረጃ አመላክቷል፡፡
በአጠቃላይ ከሁለቱም ተጠርጣሪዎች 58 ሺህ ሀሰተኛ ብር ተይዞ ምርመራ እየተካሄደ ነው ተብሏል፡፡
በሀሰተኛ ገንዘብ በመገልገል በሕገ ወጥ መንገድ ተጠቃሚ ለመሆን ወንጀል የሚፈፅሙ ግለሰቦች በሕግ አግባብ እንዲጠየቁ ለማድረግ ህብረተሰቡ እያሳየ ያለውን ተባባሪነት አጠናክሮ እንዲቀጥል ፖሊስ ጥሪ አቅርቧል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.