Fana: At a Speed of Life!

በሚቀጥሉት 10 ዓመታት ኢትዮጵያ የበለፀገች ሃገር ትሆናለች – አቶ መላኩ አለበል

አዲስ አበባ፣ ጥር 4፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ በሚቀጥሉት 10 ዓመታት የበለፀገችና ተስፋ ሰጭ ሃገር እንደምትሆን የንግድ እና ኢንዱስትሪ ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል ተናገሩ፡፡
ሚኒስትሩ በኢትዮጵያ ከቻይና አምባሳደር ዛሆ ዢዩሃን ጋር ተወያይተዋል፡፡
በውይይታቸው አቶ መላኩ አለበል ኢትዮጵያ እና ቻይና የቆየ ወዳጅነት እንዳላቸው አንስተው ግንኙነቱ አዲስ ደረጃ ላይ እንደረሰ ተናግረዋል፡፡
ይህም የሁለቱን ሃገራት ተጠቃሚነት አረጋግጧል ማለታቸውን ከንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
የቻይና መንግስትም በኢትዮጵያ ወቅታዊ የኢኮኖሚ እድገት ውስጥ ወሳኝ ሚና መጫወቱን በመጥቀስም፥ ይህ ድጋፍ ቀጣይነት ያለውና ለወደፊቱ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ገልጸዋል ፡፡
በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር ዛሆ በበኩላቸው በትግራይ ክልል የተወሰደው ህግን የማስከበር ዘመቻ ግቡን ያሳካ መሆኑን በመጥቀስ፥ የቻይና መንግስት በኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን ሙሉ ድጋፉን ያደርጋል ብለዋል፡፡
አምባሳደሩ የኮሮና ቫይረስ ዓለም አቀፍ እንቅስቃሴዎችን ቢያስተጓጉልም በሁለቱ ሃገራት መካከል ያለው ግንኙነት መቀጠሉን ጠቁመው ይህም ለሌሎች ሃገራት አርአያ ነው ብለዋል፡፡
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.