Fana: At a Speed of Life!

በሚቀጥሉት 5 ዓመታት የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ በትኩረት ይሰራል-ትምህርት ሚኒስቴር

አዲስ አበባ፣ ህዳር 9፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ አመራሮች፣ መምህራንና ሠራተኞች ጋር በትምህርት ጥራት ላይ ውይይት አካሄዱ።

ለትምህርት ጥራት መውደቅ ስር የሰደዱ በርካታ ምክንያቶች መኖራቸውን የገለፁት ሚኒስትሩ ችግሩን ለመፍታት የሁሉም ማኅበረሰብ ርብርብ እንደሚጠይቅ ጠቁመዋል።

ሚኒስትሩ በቀጣይ አምስት ዓመታት የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ በትኩረት እንደሚሰራም አመላክተዋል፡፡

ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የተለያዩ ችግሮች እንደሚስተዋሉ የገለጹ ሲሆን ፣ ዩኒቨርስቲው በጥናት የተለዩ ውስጣዊ እና ውጫዊ ችግሮችን መፍታት የሚያስችል አሰራር በመዘርጋት በልዩ ተልዕኮ ሊሰራ ይገባል ብለዋል፡፡

የውይይቱ ተሳታፊዎች በበኩላቸው ÷ የትምህርትን ጥራት ለማሻሻል የምርምር ጥራት ችግሮችን መፍታት፣ የተጀመሩ ፕሮጀክቶችን ማጠናቀቅ፣ የመምህራን ልማት ማሻሻል፣ ተቋማዊ ነፃነትን ማረጋገጥ እና የሚኒስትር መስሪያ ቤቱን አሰራር ማሻሻል እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡

ለግማሽ ቀን የተካሄደው ውይይት ሚኒስትሩ እና ሚኒስትር ዴኤታዎቹ ቀጣይ የስራ አቅጣጫዎችን በማስቀመጥ መጠናቀቁን ከትምህርት ሚኒስቴር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.