Fana: At a Speed of Life!

በሚያዚያ ወር የነዳጅ ምርቶች የችርችሮ መሸጫ ዋጋ ባለበት ይቀጥላል

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 27፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በሚያዚያ ወር ከአውሮፕላን ነዳጅ በስተቀር የሌሎች የነዳጅ ምርቶች የችርችሮ መሸጫ ዋጋ ባለበት እንደሚቀጥል የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አስታወቀ።

የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ከመጋቢት 26 እስከ ሚያዚያ 30 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ ተግባራዊ የሚሆን የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋን አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ፤ ከአውሮፕላን ነዳጅ ውጪ የሌሎች የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ባለበት ይቀጥላል።

ሚኒስቴሩ ለኢዜአ በላከው መግለጫ በሚያዚያ ወር የአውሮፕላን ነዳጅ ዋጋ በሊትር 43 ብር ከ70 ሳንቲም እንዲሸጥ የተወሰነ ሲሆን በመጋቢት ወር ሲሸጥበት ከነበረበት ዋጋ የ5 ብር ከ5 ሳንቲም ጭማሪ እንዳለው አስታውቋል።

በዓለም ገበያ ላይ የሚኖረውን የነዳጅ ዋጋ መነሻ በማድረግ እንደ አስፈላጊነቱ ማስተካከያ ሊደረግ እንደሚችልም ሚኒስቴሩ መግለጹን ኢዜአ ዘግቧል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.