Fana: At a Speed of Life!

በሚያዝያ ወር 33 ነጥብ 9 ቢሊየን ብር ገቢ ተሰበሰበ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 4፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሚያዝያ ወር ብቻ 33 ነጥብ 9 ቢሊየን ብር ገቢ መሰብሰቡን የገቢዎች ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

የገቢዎች ሚኒስትር አቶ ላቀ አያሌው በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው እንዳሰፈሩት ፥ በሚያዝያ ወር ከ35 ነጥብ 7 ቢሊየን ብር በላይ ለመሰብሰብ ታቅዶ 33 ነጥብ 9 ቢሊየን ብር ተሰብስቧል፡፡

ገቢው የተገኘው ከአገር ውስጥ ታክስ፣ ከዉጭ ንግድ ቀረጥና ታክስ ሲሆን ፥ አፈፃፀሙ ካለፈው በጀት አመት ወር ጋር ሲነፃፀር የ31 ነጥብ 19 በመቶ ዕድገት እንዳለው ተገልጿል፡፡

ሚኒስትሩ ውጤቱ መመዝገብ የቻለው የገቢዎች ሚኒስቴርና የጉምሩክ ኮሚሽን አመራሮችና ሠራተኞች በትብብርና በትጋት በመስራታቸው መሆኑን ጠቅሰው ፥ በተገኘው ስኬት የተሳተፉ አካላትን አመስግነዋል፡፡

ገቢያቸውን በወቅቱ አሳውቀው ግብር ለከፈሉ የፌደራል ግብር ከፋዮች እንዲሁም ለአጋር አካላትና ህዝቡ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.