Fana: At a Speed of Life!

በማቆያ ቦታ የሚገኙ ተጠርጣሪዎች ምንም አይነት የሰብዓዊ መብት ጥሰት እንዳልደረሰባቸው ገለጹ

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 11 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አፈጻጸም መርማሪ ቦርድ በአዲስ አበባ ከተማ የአዋጁን አፈፃፀም ተዘዋውሮ ተመልክቷል፡፡
 
የመርማሪ ቦርዱ አባላት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 የወጣቶች ማዕከልና በክፍለ ከተማው ፖሊስ መምሪያ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ህግ በመተላለፍ የተጠረጠሩ ግለሰቦች በተዘጋጀላቸው ጊዜያዊ የማቆያ ቦታዎች በአካል በመገኘት ነው ያሉበትን ሁኔታ የተመለከቱት።
 
በምልከታው በከተማ አስተዳደሩ በየደረጃው ከሚገኙ የጸጥታ አካላት ተሳትፈዋል።
 
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መርማሪ ቦርዱ አባላት በህግ ጥላ ስር የሚገኙ ተጠርጣሪዎችን ባነጋገሩበት ወቅት ተጠርጣሪዎቹ በሚገኙበት ማቆያ ቦታ ምንም አይነት የሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች ጥሰት እንዳልደረሰባቸው ገልጸዋል።
 
በሌላ በኩል በጊዜያዊ ማቆያ የሚገኙ አንዳንድ ተጠርጣሪዎች በምን ምክንያት ተጠርጥረው በህግ ጥላ ስር እንደዋሉ እንደማያውቁ ለቦርዱ አባላት መግለጻቸውን ክህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
 
በቀጣይም መርማሪ ቦርዱ በአዲስ አበባና በተለያዩ የአገሪቱ ክልሎች ተመሳሳይ ምልከታ በማድረግ የአዋጁን አፈፃፀም እንደሚከታተልና ህጋዊ ያልሆኑ አሠራሮች ማስተካከያ እንዲደረግባቸው በማድረግ የዜጎች ሰብአዊ መብት እንዲከበር አጠናክሮ እንደሚሰራ የቦርዱ ሰብሳቢ አቶ ለማ ተሰማ አስገንዝበዋል።
 
 
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.