Fana: At a Speed of Life!

በማዘጋጃ ቤት ለበዓላት ማክበሪያ ተብሎ በመጋዘን የተቀመጠ መጠነኛ ርችት በድንገት ፈንድቶ ጉዳት ሳያደርስ በቁጥጥር ስር ዋለ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 6 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በማዘጋጃ ቤት ለበዓላት ማክበሪያ ተብሎ በመጋዘን የተቀመጠ መጠነኛ ርችት በድንገት ፈንድቶ ጉዳት ሳያደርስ በቁጥጥር ስር ውሏል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ማዘጋጃ ቤት ከባፈለው ዓመት ጀምሮ አጠቃላይ የህንጻ እድሳት ስራ በመከናወን ላይ መሆኑ ተገልጿል።
በዛሬው ዕለት ከቀኑ 10፡30 በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ማዘጋጃ ቤት ለተለያዩ በዓላት ማክበሪያ ተብሎ በመጋዘን የተቀመጠ መጠነኛ ርችት በድንገት ፈንድቶ ጉዳት ሳያደርስ በቁጥጥር ስር ውሏል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የእሳት አደጋ መከላከል ባለሙያዎች ፣የፌደራል እና የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አባላት በቦታው ተገኝተው ሰራተኛው ወደ መደበኛ ስራው መመለስ እንደሚችል ያሳወቁ ሲሆን÷ የከንቲባ ጽህፈት ቤት እና የህንጻው እድሳት ስራም እንደቀጠለ መሆኑን ከከተማ አስተዳደሩ ፕሬስ ሰክሬተሪያት ቢሮ ያገኘኘው መረጃ ያመላክታል።
ህብረተሰቡም ከላይ የተጠቀሰውን እውነታ ተገንዝቦ ከተሳሳቱ መረጃዎች እራሱን እንዲያርቅ የከተማ አስተዳደሩ ጥሪ አቅርቧል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.