Fana: At a Speed of Life!

በምሥራቅ አማራ ከ11 ሺህ በላይ ጥፋተኞች ለመንግስት እጅ ሰጥተው ወደ ሕጋዊ መስመር መግባታቸው ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 13፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በምሥራቅ አማራ ከ11 ሺህ በላይ ጥፋተኞች ለመንግስት እጅ ሰጥተው ወደ ሕጋዊ መስመር መግባታቸውን የአማራ ክልል ሠላምና ጸጥታ ቢሮ ገለጸ፡፡

በምሥራቅ አማራ የፀጥታ መዋቅሩ ሀገራዊና ወቅታዊ ጉዳዮችን በብቃት ለመፈፀም የሚያስችል ውይይት እያካሄደ ነው።

በውይይቱ ላይ የአማራ ክልል ሠላምና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊ ደሳለኝ ጣሰው እንደተናገሩት፥ ጦርነቱ ካስከተለው የኢኮኖሚ ቀውስ በተጨማሪ በክልሉ አንዳንድ አካባቢዎች ያለመረጋጋትና መጠራጠር እንዲፈጠር አድርጓል።

ኢትዮጵያን ለማፍረስ፣ ክልሉን ለማተራመስና ለማዳከም እየሰሩ የሚገኙትን የህወሓትና የሸኔን ሴራ ማክሸፍ ከግንቦት 1 ጀምሮ ጥብቅ የሕግ ማስከበር ተግባር እየተሰራ መሆኑንም ኃላፊው አንስተዋል።

እየተሰሩ ባሉ የሕግ ማስከበር ተግባራት ከ11 ሺ በላይ ጥፋተኞች ለመንግስት እጅ ሰጥተው ወደ ሕጋዊ መስመር መግባታቸውም ተገልጿል።

ሁለት ሺ የሚሆኑ በሕግ ጥፋተኛ ተብለው የተወሰነባቸው ሲሆን፥ በተለያዩ ጥፋቶች እጃቸውእንደነበረበት ነው የተነገረው።

በተለያየ ጊዜ ወደ ጠላት ሊተላለፍ የነበረ ከ37 ሚሊየን ብር በላይና አንድ ሺ የሚደርስ ሕገ ወጥ የጦር መሳሪያ በሕግ ማስከበሩ ሂደት በቁጥጥር ስር ማዋሉም ተጠቁሟል፡፡

በመሆኑም የጠራ የፀጥታ መዋቅር እንዲኖር የሕግ ማስከበሩ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልና የህብረተሰቡን ሰላም ወደተሻለ ሁኔታ እንዲመጣ ክልሉ ጥረቱን አጠናክሮ ይቀጥላል ተብሏል።

በውይይቱ የፀጥታ መዋቅሩን አቅም መገንባት የሚያስችሉ ጥናቶች ይቀርባሉ፣ ቀጣይ አቅጣጫዎችም ይሰጣሉ ተብሎ ይጠበቃል።

በአንድነት ናሁሰናይ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.