Fana: At a Speed of Life!

በምሥራቅ ወለጋ ዞን ከ3 ሚሊየን ሜትር ኪዩብ በላይ የተፈጥሮ ማዳበሪያ መዘጋጀቱ ተገለፀ

ከአዲስ አበባ፣ሚያዝያ 10፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በምሥራቅ ወለጋ ዞን ለመኸር ወቅት የሚያገለግል 3 ነጥብ 5 ሚሊየን ሜትር ኪዩብ የተፈጥሮ ማዳበሪያ መዘጋጀቱን የዞኑ የግብርና ጽህፈት ቤት አስታወቀ ፡፡

በጽህፈት ቤቱ የአፈር ለምነት ማሻሻያ ቡድን መሪ አቶ ዓለሙ አስፋው እንደገለጹት÷ በአርሶ አደሮች የተዘጋጀው የተፈጥሮ ማዳበሪያ 118 ሺህ 735 ሄክታር መሬት የማልማት አቅም ያለው ነው።

በተጨማሪም ከቨርም ኮምፖስትና ከባዮ ጋዝ ተረፈ ምርት 6 ሺህ 748 ኩንታል ማዳበሪያ መዘጋጀቱን ተናግረዋል።

የተፈጥሮ ማዳበሪያ የአፈር አሲዳማነትን ስለሚቀንስ መሬቱ ለሶስት ተከታታይ ዓመታት ሌላ ማዳበሪያ ሳያስፈልገው ምርት እንደሚሰጥ ቡድን መሪው አስረድተዋል፡፡

አርሶ አደሩ ምንም ወጪ ሳያስፈልገው በአካባቢው ከሚገኙ ከእንስሳት ፍግ፣ ቅጠላ ቅጠል፣ አመድና ከተለያዩ ተረፈ ምርቶች ማዘጋጀት የሚችል በመሆኑ ጠቀሜታ እንዳለው መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.