Fana: At a Speed of Life!

በምስራቃዊ ኮንጎ የወርቅ ማዕድን ማውጫ ተደርምሶ የ50 ሰዎች ህይወት አለፈ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 2፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)በምስራቃዊ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ የወርቅ ማዕድን ማውጫ ተደርምሶ ቢያንስ የ50 ሰዎች ህይወት ማለፉን የአካባቢው ባለስልጣናት ገልጸዋል።

የአደጋው መንስኤ በአካባቢው የዘነበው ከባድ ዝናብን ተከትሎ ሰዎቹ ሲቆፍሩት የነበረው ጉድጓድ በመደርመሱ ነው ተብሏል።

በኮንጎ ቁጥጥር በማይደረግባቸው የማዕድን ማውጫዎች የሚከሰቱ አደጋዎች የተለመዱ መሆናቸው ይነገራል።

በዚህምበየዓመቱ የማዕድን ማውጫዎች በመደርመሳቸው ሰዎች ለህልፈት ይዳረጋሉም ተብሏል።

በባለፈው አመት ጥቅምት ወር በሀገሪቱ በተፈጠረ ተመሳሳይ አደጋ 16 ሰዎች ለህልፈት ሲዳረጉ÷ በዚያው ዓመት ሰኔ ወር በመዳብ እና ብረት ማዕድን ማውጫ ላይ በተከሰተ ሌላ የመሬት መንሸራተት አደጋ ደግሞ 43 ሕገ-ወጥ የማዕድን ሠራተኞች መሞታቸው የሚታወስ ነው።

ምንጭ፡- ሲጂቲኤን እና ሮይተርስ

#FBC
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.