Fana: At a Speed of Life!

በምስራቅ አፍሪካ ተወዳጅ እየሆነ የመጣው ኮሮናቫይረስ ጸጉር አሰራር

አዲስ አበባ፣ግንቦት 4፣2012(ኤፍ.ቢ.ሲ)በምስራቅ አፍሪካ የኮሮና ቫይረስን ቅርጽ የመሰለ የጸጉር አሰራር ተወዳጅነት እያደገ መምጣቱ ተነግሯል።

ለማደጉ ምክንያት ደግሞ የፀጉር አቆራረጥ ቅርፁን ለመፍጠር እና ከሌሎች አሠራር ይልቅ ዋጋው በ90 በመቶ ርካሽ በመሆኑ ነው ተብሏል።

በዚህም ኮሮናቫይረስን የሚመስሉ ልዩ ልዩ የፀጉር አሠራሮች በምሥራቅ አፍሪካ በመነቃቃት ላይ ናቸው ተብሏል።

ቫይረሱን የመሰለው አሰራር መነቃቃት ከወረርሽኙ ጋር ተያይዞ ከተጣሉ ገደቦች ጋር የተዛመዱ የገንዘብ ትግሎች ጋር የተዛመደ ከመሆኑም ባለፈ ኮቪድ -19 እውን ነው የሚለው ግንዛቤን ከፍ ከማድረግ ጋር የተያያዘ መሆኑም ተጠቁሟል።

ይህ አይነቱ የጸጉር የአሰራር ፍላጎት በአህጉሪቱ እየጨመረ በመምጣቱ፥ በዚህ ዘይቤ የተዋጣለት እውነተኛ እና ሰው ሠራሽ ፀጉር ከቻይና ፣ ህንድ እና ብራዚል ካሉ ስፍራዎች ወደ ገበያ እየገባ መሆኑም ነው የተነገረው።

በኬንያ ዋና ከተማ ናይሮቢ ኪቤራ በተባለው መንደር ውስጥ ፀጉር አስተካካይ የሆነችው ሳሮን ሬፋ፥ የወጣት ልጃገረዶች ፀጉር “ኮሮናቫይረስ የፀጉር አሠራር” ተብሎ የሚጠራውን አሰራር መስራት መጀመሯን ገልጻለች።

አያይዛም ምንም እንኳን ብዙ ልጆች እጆቻቸውን በሳኒታይዝር ቢያጸዱም እና የፊት ጭምብልን ለማድረግ ፍላጎት ቢኖራቸውም አንዳንድ ትልልቅ ሰዎች ኮሮናቫይረስ እውነት ነው ብለው እንደማያምኑ  ተናግራለች።

በዚህም ብዙ አዋቂዎች ወረርሽኙን ለመከላከል የሚደረጉትን ጥንቃቄዎች ተግባራዊ አያደርጉም ስለሆነም ግንዛቤውን ለማሳደግ እኛ የኮርና የፀጉር አሠራር አመጣን ብላለች ፡፡

ምንጭ፡-https://news.sky.com/

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!

https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.