Fana: At a Speed of Life!

በምስራቅ ወለጋ ዞን ከ28 ሺህ በላይ የተለያዩ ጥይቶች ተያዙ

አዲስ አበባ፣ ጥር 9፣ 2014 (ኤፍ ቢሲ) በምስራቅ ወለጋ ዞን ጉቡ ሰዮ ወረዳ አኖ ከተማ በህገ ወጥ መንገድ ሲዘዋወሩ የነበሩ ከ28 ሺህ በላይ የተለያዩ የጦር መሳሪያዎች ጥይቶች ተያዙ።

ጥይቶቹ ለአሸባሪው ሸኔ ሊተላላፉ እንደነበር ከኦሮሚያ ክልል ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ጥይቶቹ የተያዙት በቤት መኪኖች እና በህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪዎች ላይ በተደረገ ፍተሻ መሆኑ ታውቋል፡፡

በተለይም ጥይቶቹን የጫነው አይሱዙ መኪና ከአዳማ ከተማ ተነስቶ በምስራቅ ወለጋ ዞን ጉቡ ሰዮ ወረዳ አኖ ከተማ ሽንኩርት ጭኖ ሲንቀሳቀስ በህብረተሰቡ ጥቆማ ሊያዝ ችሏል፡፡

የተያዙትም የብሬል ጥይት 22 ሺህ 132 እና 5 ሺህ 895 የክላሽ ጥይቶች መሆናቸው ተገልጿል፡፡

ህብረተሰቡ የጸረ ሰላም እንቅስቃሴዎችን ሲመለከት የተለመደውን ትብብርና ጥቆማ አጠናክሮ እንዲቀጥል እና ከጸጥታ ሃይሎች ጋር ተባብሮ እንዲሰራ ቢሮው ጥሪ አቅርቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.