Fana: At a Speed of Life!

በምስራቅ ጎጃም ዞን እስካሁን ከ177 ሺህ ሄክታር በላይ ሰብል ተሰብስቧል

አዲስ አበባ፣ ህዳር 10፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሰብል አሰባሰብ ወቅት ምርት እንዳይባክን በትኩረት እየተሰራ መሆኑ የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ አስታውቋል፡፡
በምስራቅ ጎጃም ዞን በ2013/14 የምርት ዘመን 607 ሺህ 141 ሄክታር መሬት በዘር መሸፈኑን የገለጸው ቢሮው÷ እስካሁን 177 ሺህ 517 ሄክታር ሰብል መሰብሰቡን ጠቁሟል፡፡
 
በተለይ ዋና ዋና ሰብሎች ጤፍ፣ ስንዴ፣ በቆሎና ሌሎች በክላስተር አደረጃጀት ማልማት በመቻሉ በምርትና ምርታማነት ላይ ከፍተኛ ውጤት ይገኛል ተብሎ እንደሚጠበቅ ተመላክቷል፡፡
 
በዞኑ የዘማች አርሶ አደሮች ሰብል በህብረተሰቡ ተሳትፎ እስካሁን 402 ሄክታር በዘር የተሸፈነ መሬት የተሰበሰበ ሲሆን ÷ምርት እንዳይባክን በጥንቃቄ እየተሰራ ነው ተብሏል፡፡
 
በዞኑ በተለያዩ ወረዳዎች 18 ኮምባይነር ገብቶ የደረሱ ሰብሎችን እየሰበሰበ መሆኑን ከአማራ ክልል ግብርና ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
 
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.