Fana: At a Speed of Life!

በምዕራብ ሸዋ ዞን በትራፊክ አደጋ አባትና ልጅን ጨምሮ የ3 ሰዎች ህይወት አለፈ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 11፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) በምዕራብ ሸዋ ዞን ኤጀሬ ወረዳ በዛሬው ዕለት በደረሰ የትራፊክ አደጋ የሶስት ሰዎች ህይወት አለፈ።

በትራፊክ አደጋው ህይወታቸው ካለፈ ሰዎች በተጨማሪ አምስት ሰዎች የአካል ጉዳት እንዳጋጠማቸው ነው የተነገረው።

ይህ አደጋ ዶልፊን ተሽከርካሪ ከጭነት አይሱዚ ተሽከርካሪ ጋር በኤጀሬ ወረዳ ጭሪ ቀበሌ በመጋጨታቸው ያጋጠመ መሆኑን  የኤጀረ ወረዳ የትራፊክ አስተባባሪ ሳጅን ለማ ጉታ ገልፀዋል።

በዚህ የትራፊክ አደጋ አባት እና ልጅ ህይወታቸውን ማጣታቸው ከዞኑ ኮሙዩኒኬሽን ፅህፈት ቤት የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

የዛሬውን የትራፊክ አደጋ ጨምሮ በሳምንቱ ለሶስተኛ ጊዜ በዞኑ በደረሰው የትራፊክ አደጋ በአጠቃላይ የ11 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ የአካል ጉዳት እና የንብረት መውደም አጋጥሟል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፦https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.