Fana: At a Speed of Life!

በምዕራብ ጎንደር ዞን በ257 ሚሊየን ብር የተገነቡ የልማት ተቋማት ተመረቁ

አዲስ አበባ ፣ሐምሌ  25 ፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በምዕራብ  ጎንደር  ዞን ከ257 ሚሊየን ብር በሚበልጥ ወጪ የተገነቡ  መሰረተ  ልማቶች  ተመረቁ ።

በምርቃት ስነ ስርዓቱ  ላይ  የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር  አቶ  ተመስገን ጥሩነህ፣ የክልሉ ብልፅግና ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ አገኘሁ  ተሻገር ፣ የክልሉ ምክር ቤት ዋና አፈጉባኤ ወይዘሮ ወርቅሰሙ  ማሞና  ሌሎችም  የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል።

በዞኑ ተገንብተው ከተመረቁት መሰረተ ልማቶች  መካከል  የመተማ  የመጀመሪያ ደረጃ  ሆስፒታል  ማስፋፊያ ግንባታ፣ የቋራና አብርሃ ጅራ  የመጀመሪያ  ደረጃ ሆስፒታሎች ይገኙበታል ተብሏል።

ከዚያም ባለፈ ሁለት የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች፣ አራት የመጀመሪያ ደረጃ  ትምህርት ቤቶች፣ የደም ባንክ አገልግሎት ማዕከልና የመንገድ መሰረተ ልማት ዝርጋታዎች በአመራሮቹ ተመርቀው ለአገልግሎት ክፍት ሆነዋል።

በአሁኑ ወቅትም ከነዋሪዎቹ ጋር በገንዳ ውሃ ከተማ ውይይት እየተደረገ ሲሆን÷ አመራሮቹ ቀጣይ የልማት አቅጣጫ ያስቀምጣሉ  ተብሎ  እንደሚጠበቅ  ኢዜአ  ዘግቧል ።

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.