Fana: At a Speed of Life!

በሠላም መልሶ ግንባታና በሕግ ማስከበር ላይ ያተኮረ አገር አቀፍ ውይይት ተካሄደ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 15 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በሠላም መልሶ ግንባታና በሕግ ማስከበር ላይ ያተኮረ አገር አቀፍ ውይይት በአዲስ አበባ ተካሄደ።

በስትራቴጂክ ጉዳዮች ኢንስቲትዩት በተዘጋጀው በዚህ ውይይት የፖለቲካ ፓርቲዎች ተወካዮች፣ ምሁራን፣ የሲቪክ ማኅበራት ተወካዮች፣ የፌዴራልና የክልል ተወካዮች ተሳትፈዋል።በመድረኩ ሶስት የመነሻ ጥናታዊ ጽሁፎች ቀርበው ውይይት ተካሂዶባቸዋል።

በውይይቱ የተገኙ ምክረ ሀሳቦች ለመንግስት በግብዓትነት እንደሚውሉም ተጠቁሟል።

በድህረ ግጭት የሚታዩ ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊና ሠብዓዊ ጉዳዮችን ማረም የሚያስችል ጥናታዊ ጽሁፍ በመድረኩ እንደቀረበ ኢዜአ ዘግቧል።

ኢንስቲትዩቱ በኢትዮጵያ ሠላምና መረጋጋት ይበልጥ እንዲጎለብት የሚያግዙ የግንዛቤና የክህሎት ማጎልበቻ ስልጠናዎችን እንደሚሰጥ ይታወቃል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.