Fana: At a Speed of Life!

በሣምንቱ ከ10 ሺህ ቶን በላይ ሰብዓዊ ዕርዳታ ወደ ትግራይ ክልል ደርሷል – የዓለም የምግብ ፕሮግራም

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 15፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በዚህ ሣምንት ከ10 ሺህ ቶን በላይ የምግብ እና የነፍሥ አድን አቅርቦቶች ትግራይ ክልል መድረሳቸውን የዓለም የምግብ ፕሮግራም አስታወቀ፡፡

የሰብዓዊ ዕርዳታ አቅርቦቶቹ በታጀቡ 163 የጭነት ተሽከርካሪዎች ሁለት ጊዜ ወደ ትግራይ ክልል መጓጓዛቸውን የዓለም የምግብ ፕሮግራም በመረጃው አመላክቷል፡፡

የዓለም ምግብ ፕሮግራም አጋሮቹን አመስግኖ ከፈረንጆቹ ሐምሌ ወር 2021 ጀምሮ ትግራይ ክልል የሰብዓዊ ዕርዳታ አቅርቦት ጭነው ከደረሱት የጭነት ተሽከርካሪዎች ከ100 በላይ የሚሆኑት አቅርቦቶቹን ወደ ክልሉ አድርሰው መመለሳቸውንም አስታውቋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.