Fana: At a Speed of Life!

በሦስት ደቂቃ ውስጥ ዓይንን በማየት ኮቪድ 19ኝን የሚመረምር የሞባይል መተግበሪያ ተሰራ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 5፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) መሰረቱን ጀርመን ያደረገ ኩባንያ በሦስት ደቂቃ ውስጥ ዓይንን ፎቶ በማንሳት /ስካን/ በማድረግ ኮቪድ19ኝን የሚመረምር የሞባይል መተግበሪያ /አፕሊኬሽን/ መስራቱን አስታወቀ፡፡

ይህ ሦስት ደቂቃ ይወስዳል የተባለው መመርመሪያ 95 በመቶ ውጤታማ ነው ተብሏል፡፡

መተግበሪያው ዘመናዊ ተንቀሳቃሽ ስልኮችን በመጠቀም ቫይረሱን እንደሚለይ ተገልጿል፡፡

እስካሁን በ70 ሺህ ግለሰቦች ላይ እንደተሞከረም ተሰምቷል፡፡

በደቂቃዎች ውስጥ ስካን በማድረግ በሚሊየን የሚቆጠር ውጤት ይሰጣል ተብሏል፡፡

ይህም እንደ እግር ኳስ ባሉ ህዝብ በብዛት በሚሰበሰብባቸው ዝግጅቶች ላይ መተግበሪያውን መጠቀም እንደሚያስችልም ነው የተገለጸው፡፡

መተግበሪያውን ለንግድ አላማ መጠቀም ለሚፈልጉ ኩባንያዎች በወር 570 ዶላር መክፈል ይጠበቅባቸዋል ተብሏል፡፡

ኩባንያው ጊዜውን በትክክል ባያስቀምጥም ለግለሰቦች ለማዳረስ ዕቅድ መያዙንም ሬውተርስ ዘግቧል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.