Fana: At a Speed of Life!

በሩብ ዓመቱ ከ720 ሚሊየን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ ዕቃዎች እና ገንዘቦች በቁጥጥር ዋሉ

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 4 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በ2013 በጀት ዓመት በገቢና በወጪ ኮንትሮባንድ 720 ሚሊየን 865 ሺህ 714 ብር ግምታዊ ዋጋ ያላቸው ልዩ ልዩ ዕቃዎች እና የተለያዩ ሀገራት ገንዘቦች መያዛቸውን ገቢዎች ሚኒስቴር አስታወቀ።
ከዚህ ውስጥ 568 ሚሊየን 754 ሺህ 537 ብር የሚገመተው የጉምሩክ ስነ-ስርዓት ሳይፈፀምባቸው ወደ ሀገር ለማስገባት ሙከራ ሲደረግ የተያዙ ዕቃዎችና በህገወጥ መንገድ ሲዘዋወሩ ተያዙ ገንዘቦች ናቸው ተብሏል፡፡
ከዚያም ባለፈ ግምታዊ ዋጋቸው 152 ሚሊየን 111 ሺህ 176 ብር የሚሆነው ከሀገር ሊወጣ የነበረ የኮንትሮባንድ ዕቃ እና ህገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውር መሆኑ ተመላክቷል፡፡
ከተያዙት የገቢ ኮንትሮባንድ ዕቃዎች ውስጥ ተሽከርካሪ፣ አዳዲስ አልባሳት እና የምግብና መጠጥ ምርቶች ዋና ዋናዎቹ መሆናቸው ተነግሯል፡፡
በወጪ ኮንትሮባንድ ምድብ በቁጥጥር ስር ከዋሉ ዋና ዋና የኮንትሮባንድ ዕቃዎች አደንዛዥ ፅፅ የመጀመሪያ ደረጃ ላይ የሚገኝ ሲሆን ÷ማዕድን እና ህገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውር እንደቅደም ተከተላቸው የሁለተኛ እና ሶስተኛ ደረጃ መያዛቸው ተገልጿል፡፡
ከዚያም ባለፈ በሩብ ዓመቱ በኮንትሮባንድ ንግድ ተሳትፈዋል ተብለው የተጠረጠሩ 270 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘኘው መረጃ ያመላክታል።
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.