Fana: At a Speed of Life!

በሩብ ዓመቱ የ929 ሰዎች ሕይወት በትራፊክ አደጋ አልፏል — ትራንስፖርት ሚኒስቴር

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 12 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በ2013 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት በሀገር አቀፍ ደረጃ የ929 ሰዎች ሕይወት በትራፊክ አደጋ ማለፉን የትራንስፖርት ሚኒስቴር አስታወቀ።

ሚኒስቴሩ 15ኛውን ዓለም አቀፍ የመንገድ ትራፊክ አደጋ ተጎጂዎች መታሰቢያ ቀንን አስታውሶ ውሏል።

ዕለቱ በኢትዮጵያ ለ13ኛ ጊዜ ነው ታስቦ የዋለው።

በዕለቱም 2 ሺህ 512 ሰዎች ላይ ከባድና ቀላል የአካል ጉዳት መድረሱ ተገልጿል።

የመታሰቢያ መርሃ ግብሩ “በትራፊክ አደጋ ምክንያት ሕይወታቸውን ያጡና ጉዳት የደረሰባቸውን ወገኖች እናስታውስ፣ እንደግፍ፣ ለውጥ እናምጣ” በሚል መሪ ሀሳብ ሲከናወን ባለድርሻ አካላትና የትራፊክ አደጋ ተጎጂዎችና ቤተሰቦቻቸው ታድመዋል።

የትራንስፖርት ሚኒስትሯ ዳግማዊት ሞገስ የመታሰቢያ መርሃ ግብሩ ዓላማ በትራፊክ አደጋ ሕይወታቸው ያለፈ፣ ጉዳት የደረሰባቸውንና በአደጋው ቤተሰቦታቸውን ያጡ ወገኖችን ማሰብ እንደሆነ ተናግረዋል።

ሚኒስቴሩ ለኅብረተሰቡ ግንዛቤ ከመፍጠር ባሻገር ከፌደራል ፖሊስ ጋር በመሆን ሕግ የማስከበር ሥራ እየሰራ መሆኑንም ገልፀዋል።

በዓለም ላይ በትራፊክ አደጋ በየዓመቱ ከ1 ነጥብ 3 ሚሊዮን በላይ ሰዎች ሕይወት ሲያልፍ ከ50 ሚሊየን በላይ የሚሆኑት ደግሞ ለከባድና ቀላል የአካል ጉዳት እንደሚዳረጉ መረጃዎች ያመላክታሉ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.