Fana: At a Speed of Life!

በክልሉ ግብርናውን ለማዘመን 17 መርሐ ግብሮች ተመርጠው እየተተገበሩ ነው – አቶ ሽመልስ አብዲሳ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 26፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ግብርናውን ለማዘመን 17 መርሐ ግብሮች ተመርጠው እየተተገበሩ መሆኑን የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ ገለፁ።

በኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ የተመራ ልዑክ በሞጆ ከተማ የሚገኝ የተለያዩ የልማት ፕሮጀክቶችን ጎብኝተዋል።

በጉብኝት መርሐ ግብሩ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምክትል አፈ-ጉባኤ ወይዘሮ ሎሚ በዶን ጨምሮ የፌደራል እና የክልሉ የተለያዩ የሥራ ሃላፊዎች ተሳትፈዋል፡፡

በጉብኝቱ ወቅት ርዕስ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ እንደገለፁት÷ ለኢትዮጵያ እድገት ወሳኝ የሆነውን ግብርናን ማዘመን ጊዜው የሚፈልገው ስራ ነው።

በአሁኑ ወቅት 1 ነጥብ 3 ቢሊየን የቡና ችግኝ በክላስተር ለማልማት የዝግጅት ስራ እየተጠናቀቀ መሆኑን ጠቅሰው÷ ባለፉት ሶስት ዓመታት ከ2 ነጥብ 9 ቢሊየን በላይ የቡና ችግኞች መተከላቸውን ተናግረዋል፡፡

17 ሺህ የውሃ መሳቢያ ሞተሮች ለአርሶ አደሩና አርብቶ አደሩ መሰራጨታቸውን የገለጹት ርዕሰ መስተዳድሩ÷ በቀጣይ 20 ሺህ የውሃ መሳቢያ ሞተሮችን ለማሰራጨት ታቅዷልም ብለዋል፡፡

በዘንድሮው ዓመት ከ600 ሺህ ሄክተር በላይ ስንዴን በመስኖ ማልማት መቻሉን እና በመጪው የበጀት ዓመት ከ1 ሚሊየን ሄክታር በላይ መሬት በመስኖ ስንዴ ለማልማት ዝግጅት እየተደረገ መሆኑንም አመልክተዋል።

ለመጪው ክረምት ከ4 ነጥብ 6 ቢሊየን በላይ ለተለያየ አገልግሎት የሚውሉ ችግኞችን ለመትከል ዝግጅት መጠናቀቁን ጠቁመው÷ ምክር ቤቱ ድጋፍና እገዛ ሊያደርግል ይገባልም ነው ያሉት፡፡

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባኤ ወይዘሮ ሎሚ በዶ በበኩላቸው÷ በምስራቅ ሸዋ ዞን የታዩ የልማት ስራዎች እና የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር ዝግጅቶች የልማት ስራዎች ተስፋ ሰጪ ናቸው ብለዋል።

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.