Fana: At a Speed of Life!

በሰሜን ሸዋ ዞን በቀዳማዊት እመቤት ጽ/ቤት የተገነባው ኢፋ ሰላሌ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተመረቀ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 19 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን በቀዳማዊት እመቤት ጽህፈት ቤት የተገነባው ኢፋ ሰላሌ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተመረቀ።
 
በውጫሌ ወረዳ ቦሶቄ ጃቴ ቀበሌ ግንባታው ተጠናቆ አግልግሎት መስጠት የጀመረውን የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቱ ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው መርቀው ከፍተውታል።
 
በተጨማሪም የኦሮሚያ ክልል የትምህርት ቢሮ አመራሮችን ጨምሮ የትምህርት ቤቱ ማህበረሰብና ተማሪዎች በምርቃት ስነ ስርዓቱ ላይ መገኘታቸው ነው የተገለጸው፡፡
 
ትምህርት ቤቱ 16 የመማሪያ ክፍሎችን ጨምሮ ቤተ መጻህፍት እና የሰራተኞች ቢሮን ያካተተ መሆኑ ተጠቁሟል፡፡
 
ከ13 ነጥብ 7 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የተደረገበት ትምህርት ቤቱ 800 ተማሪዎችን የመቀበል አቅም እንደሚኖረው ተነግሯል።
 
በአሁኑ ወቅትም 158 ተማሪዎችን ተቀብሎ እያስተማረ እንደሚገኝ ነው የታወቀው፡፡
 
ጽህፈት ቤቱ በመላ ሃገሪቱ 20 የሚሆኑ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችን ለማስገንባት አቅዶ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል ተብሏል፡፡
 
የቀዳማዊት እመቤት ጽህፈት ቤት ሊሰራቸው ካቀዳቸውና ግንባታቸው ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት የጀመሩት የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በሀገሪቱ የተለያዩ ከተማዎች የሚገኙ ናቸው።
 
የአሁኑን ጨምሮ አምስት ትምህርት ቤቶች አገልግሎት መስጠት መጀመራቸው ነው የተገለጸው፡፡
 
በፍሬህይወት ሰፊው
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.