Fana: At a Speed of Life!

በሰሜን የሃገሪቱ ክፍል መንግሥት በሃላፊነት ስሜት የሚያካሂደው የሰብዓዊ ድጋፍ ሊሸፈን አይገባም- አቶ ደመቀ መኮንን

አዲስ አበባ፣ መስከረም 11፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን 76ተኛ የተ.መ.ድ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ ኒው ዮርክ አሜሪካ የገቡ ሲሆን፤ ከጉባኤው ጎን ለጎን ከዓለም ምግብ ፕሮግራም ዋና ዳይሬክተር ሚስተር ዴቪድ ባስሌይ ጋር ተገናኝተው ተወያይተዋል።

በውይይታቸው በሰሜን የሃገሪቱ ክፍል ፥ መንግሥት በሃላፊነት ስሜት የሚያካሂደው የሰብዓዊ ድጋፍ ጥረት መሬት ላይ ያለ እውነት በመሆኑ ሊሸፈን እንደማይገባው አሳስበዋል።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሰብዓዊ ስጋቶችን ደረጃ በደረጃ ለመቅረፍ መንግስት እየወሰደ ያለውን እርምጃ በዝርዝር ያስረዱ ሲሆን፤ በተደጋጋሚ የሰብዓዊ ድጋፍ አሰጣጥ ዙሪያ የሚገጥሙ ችግሮችን አብራርተዋል።

በሰብዓዊ ዕርዳታ ዙሪያ የሚስተዋሉ ክፍተቶችን ለመቅረፍ ከዓለም የምግብ ፕሮግራም ጋር መንግሥት በቅንጅት እየተንቀሳቀሰ መሆኑን በመጠቆም፤ በቀጣይም ውጤታማ በሆነ አግባብ ትብብሩ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልፀዋል።

የሰብዓዊ ድጋፍ አሰጣጥን በማመቻቸት ረገድ በመንግስት ላይ ሚዛናቸውን ያልጠበቁ እና ትክክለኛ ያልሆኑ ክሶች ተደጋግመው እንደሚነሱ በማስታወስ፤ በመንግስት በኩል የሚደረገው ሰብዓዊ ድጋፍ በችግሩ ተጎጂ ለሆኑ ወገኖች በሙሉ ተደራሽ ያደረገ መሆኑን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አረጋግጠዋል።

በተመሣሣይም አቶ ደመቀ መኮንን ከቬንዙዌላ የውጭ ግንኙነት ሚኒስትር ፌሊክስ ራሞን ፕላስሴሲያ ጎንዛሌዝ ጋር በሁለቱ አገራት መካከል ያለውን ታሪካዊ ግንኙነት በሚያጠናክሩ ጉዳዮች ዙሪያ ኒውዮርክ ላይ መክረዋል።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንንበቀጣይ በሃገራቱ መካከል ያለውን የሁለትዮሽ ግንኙነት ለማጠናከር እና የትብብር ማዕቀፍ ለማስፋት ትርጉም አዘል ስራዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ   ማለታቸውን ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

0
People Reached
37
Engagements
Boost Post
33
4 Shares
Like

 

Comment
Share
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.