Fana: At a Speed of Life!

በሰርግ ላይ ለደስታ የተተኮሰው ጥይት የ16 ዓመቱን ታዳጊ ህይወት ቀጠፈ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 9፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአማራ ክልል ምስራቅ ጎጃም ዞን አነደድ ወረዳ በተከናወነ ሰርግ ላይ ለድምቀት የተተኮሰው ጥይት የ16 ዓመቱን ታዳጊ ህይወት ቀጥፏል።

በትናንትናው ዕለት ከቀኑ 9 ሰዓት ላይ አነደድ ወረዳ የወቢ እነችፎ ቀበሌ በነበረው ሰርግ ላይ የታደሙ የአካባቢው ነዋሪዎች ሙሽራው ሲወጣ ደስታቸውን በሚገልፁበት ወቅት በተተኮሰው ጥይት የታዳጊው ህይወት ማለፉን ተነግሯል።

ታዳጊው እንጨት ላይ ወጥቶ የሰርግ ስነ ስርዓቱን እየተከታተለ በነበረበት ወቅት በጀርባ ቀኝ ትከሻው ላይ በአንድ ጥይት ተመቶ ህይወቱ ወዲያውኑ ማለፉን ከወረዳው ኮሙዩኒኬሽን ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

በጉዳዩ የተጠረጠሩ ሁለት የሚሊሻ አባላትም በቁጥጥር ስር ውለው ምርምራ እየተካሄደባቸው ሲሆን፥ አንድ ያልተያዘ ሚሊሻ ደግሞ ክትትል እየተደረገበት መሆኑ ተጠቁሟል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.