Fana: At a Speed of Life!

በሰቆጣ ለሚገኙ ተፈናቃዮች 2 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር ግምት ያለው የዓይነት ድጋፍ ተደረገ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 8፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ አፍሪካ “ኢስተርን ኬፕ ኡምታታ ከተማ የሚኖሩ ትውልደ ኢትዮጵያውያን ከአዲስ አበባ አማራ ወጣቶች ጋር በመተባበር በአማራ ክልል ዋግኽምራ ዞን በሰቆጣ ከተማ ለሚገኙ ተፈናቃዮች 2 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር ግምት ያለው የቁሳቁስ ድጋፍ አደረጉ፡፡

በአዲስ አበባ የአማራ ወጣቶች ማኅበር ፕሬዚዳንት ዘነበ በለጠ ÷ በደቡብ አፍሪካ “ኢስተርን ኬፕ ኡምታታ” ከተማ የሚኖሩ ትውልደ ኢትዮጵያውያን 1 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር ግምት ያለው የስንዴ ዱቄት ድጋፍ ማድረጋቸው ተናግረዋል፡፡

በአዲስ አበባ የአማራ ወጣቶች ማኅበርም ከተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች ያሰባሰበውን የትምህርት መማሪያ ቁሳቁስ እና አልባሳት እንዲሁም የንፅህና መጠበቂያን ጨምሮ ፓስታ እና ማካሮኒ ድጋፍ ማድረጉንም ገልጸዋል፡፡

በቅድስት ተሥፋዬ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.