Fana: At a Speed of Life!

በሰበታ ከተማ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ11 ሰዎች ህይወት አለፈ

አዲስ አበባ፣ ጥር 21፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በሰበታ ከተማ በዛሬው እለት በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ11 ሰዎች ህይወት ማለፉ ተገለፀ።

የትራፊክ አደጋው በዛሬው እለት ከቀኑ 8 ሰዓት አካባቢ መድረሱንም ከሰበታ ከተማ አስተዳደር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

አደጋውም በሰበታ ከተማ ዲማ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በተለምዶ ሀይሩፍ ተብሎ የሚጠራ የህዝብ ማመላለሻ ሚኒባስ ተሽከርካሪ ከሲኖ ትራክ ጋር በመጋጨቱ የተፈጠረ ነው።

በአደጋውም የ11 ሰዎች ህይወት ወዲያውኑ ሲያልፍ፤ 7 ሰዎች ላይ ደግሞ ከባድ የመቁሰል አደጋ መድረሱን የሰበታ ከተማ ጤና ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አብዱራዛቅ አህመድ ተናግረዋል።

በአሁኑ ወቅትም ከአደጋው የተረፉ ሰዎች የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው መሆኑንም አስታውቀዋል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.